Categories:
የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ የጎንደር ክላስተር የክትትልና ግምገማ ቡድን በማእከላዊ ጎንደር ዞን በተመረጡ ተቋማትን የ5 ወር እቅድ አፈጻጸምን መሰረት ያደረገ የድጋፍና ክትትል ስራ በመስራት ላይ ነው።
ከተደገፉት ተቋማት መካከል የዞኑ ግብርና መምሪያ አንዱ ሲሆን ጠቅላላ የምርትና ምርታማነትን የሚያሳድጉ ግብዓቶችንና ጸረ ተባይና ጸረ አረም ኬሚካሎችን ማቅረብና ማሰራጨት፣ የአፈር ለምነትን ማሻሻል፣ የቴክኖሎጅ ግብዓቶችን ማቅረብና ማሰራጨት፣ ዘላቂ የተፈጥሮ ሃብት ልማትና አጠቃቀምን ለማረጋገጥ በርካታ አበረታች ስራወች በመስራት በኩል በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ቡድኑ አረጋጝጧል።
በተለይም ከበጋ መስኖ ስንዴ ተግባራት ጋር በተያያዘ 18311 ሄክታር መሬት በዘር በመሸፈን ከእቅድ በላይ መፈጸም መቻሉ፣ የተፋሰስ ስራን ዉጤታማ ለማድረግ በአዲስና በነባር 815 ተፋሰሶችን ለማልማት የቅድመ ዝግጅት ስራወችን ማጠናቀቁ እንዲሁም ከእንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ተግባራት አንጻር በርካታ ስራዎችን ከእቅድ በላይ መፈጸም የቻለ መሆኑ መምሪያውን የተሻለ አፈጻጸም እንዲኖርው ያደረገ አድርጓል።
ሌላው ድጋፍና ግምገማ የተደረገለት ተቋም የዞኑ ትምህርት መምሪያ ሲሆን ከመምሪያ ሃላፊወች፣ ከተቋሙ ማናጅመንት አባላት እና ከማእከላዊ ጎንደር ዞን ፕላንና ልማት ቡድን ባለሙያወች ጋር በጋራ በመሆን የተቋሙን የእቅድ አፈጻጸም በዝርዝር ማየትና መገምገም ተችሏል።
በግምገማውም መምሪያው ሊሰራቸው ሲሚገባ በውቅታዊ ችግሮች ምክንያት ያልሰራቸው በርካታ ስራዎች መኖራቸውን ማየት ተችሏል። በመሆኑም ጠንካራ አፈጻጸሞች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ፣ የአፈጻጸም ድክመት የታየባቸዉ ተግባራት ላይ ትኩረት ተደርጎ እንዲሰራ፡ እንዲሁም በቀጣይ ትኩረት ሊያደርግባቸዉ የሚገቡ ተግባራት ላይ አስተያየት በመስጠት በጋራ መግባባት የድጋፍ