Categories:
“ፕሮጀክቶች የልማት ግቦችንና ኢላማዎችን ማስፈጸሚያ መሳርያዎች ናቸው”
ደመቀ ቦሩ(ዶ/ር)
የክልሉን የፕሮጀክት አስተዳደርና አመራር ስርአት ረቂቅ አዋጅ ለማዳበር የሚያስችል ግብአት ማሰባሰቢያ ወርክሾፕ ተካሄደ፥
+++
ግንቦት 23/2017 ዓ.ም
ባህርዳር
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፕላንና ልማት ቢሮ በፕሮጀክት አስተዳደርና አመራር ረቂቅ አዋጅ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር አድርጓል።
የምክክር መድረኩ አላማ በቀጣይ ለክልሉ ም/ቤት ባጀንዳነት አቅርቦ ለማጸደቅ የተዘጋጀውን የፕሮጀክት አስተዳደርና አመራር አዋጅ በቅርጽና በይዘት የተሟላ እንዲሆን ግብአት ማሰባሰብ መሆኑን መድረኩን የከፈቱት የቢሮው ሀላፊ ደመቀ ቦሩ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
“ፕሮጀክቶች የልማት ግቦችንና ኢላማዎችን ማስፈጸሚያ መሳርያዎች ናቸው” ያሉት ደመቀ ቦሩ (ዶ/ር) ለፕሮጀክቶች የተመደበ በጀት ባግባቡ ጥቅም ላይ ውሎ በሚፈለገው ፍጥነትና ጥራት ተጠናቀው የሚጠበቅባቸውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትሩፋት ማስገኘት አለባቸው ያሉ ሲሆን ለዚህም ክልላዊ የፕሮጀክት ማስፈጸሚያ ህግ ያስፈልጋል ብለዋል።
መንግስት በፖሊሲ ደረጃ የሚያስቀምጣቸው የልማት ግቦችና ኢላማዎች የሚተገበሩት በፕሮጀክቶች አማካኝነት በመሆኑ ታቅደው እስኪፈጸሙ ድረስ ባግባቡ መመራት አለባቸው ያሉት የፕላንና ልማት ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ ጥላሁን ወርቅነህ ለዚህም ህጋዊ አሰራር ማስቀመጥ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል
የተዘጋጀውን የአዋጁን ረቂቅ የፍትህ ቢሮ የህግ ባለሙያ አቶ ጸሀይነህ አጥናፉ በጽሁፍ አቅርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፥
ክልሉ ፕሮጀክቶችን የሚያስተዳድርበት አዋጅ ሳይኖረው በመቆየቱ ችግሮች ሲስተዋሉ የቆዩ መሆኑን የመድረኩ ተሳታፊዎች አንስተው አሁን ግን በዚህ ደረጃ አዋጅ እንዲውጣና እንዲመራ ግብአት መሰብሰቡ ተገቢ ነው ብለዋል።
ተሳታፊወቹ ፕሮጀክቶች ሲታቀዱ ጀምሮ እስኪጠናቀቁ ድረስ የሚኖራቸውን አፈጻጸም ማስተዳደርና መምራት የሚያስችል አዋጅ ጸድቆ እንዲወጣ ጠቃሚ ነው ያሉትን ሀሳብ ስጥተዋል።
በመጨረሻም የክልሉን ዘላቂ ልማት የሚያረጋግጥ ፍትሃዊ ፣ውጤታማና ቀልጣፋ የፕሮጀክት አስተዳደርና አመራር ስርዓት እንዲኖረን የሚያስችል አዋጅ ለማዘጋጀት በመድረኩ የተገኝው ግብዓት ጠቃሚ መሆኑን የቢሮ ሀላፊው ገልጸውና ተሳታፊውን አመስግነው ስብሰባው ተጠናቋል።
ምርምር፣ ፈጠራ፣ ትጽእኖ!
“Researching, Innovating, influencing”
‎x-account:- https://x.com/logout
‎gmail address:- plananddevelopmentbureau@gmail.com