የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ክልሉን የዘመናዊ መረጃ አስተዳደር ስርአት ባለቤት ለማድረግ እየሰራ መሆኑ ተገለጸ
ግንቦት 25/2017
የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ የክልሉን የዘነናዊ መረጃ ስትራቴጂ አዘጋጅቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር ገመገመ።
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የፕላንና ልማት ቢሮ ሀላፊ ደመቀ ቦሩ (ዶ/ር) “የመድረኩ አላማ ቢሮው ረጅም ጊዜ ወስዶ ያዘጋጀው የዘመናዊ መረጃ አስተዳደር ስርአት ክልሉ የሚያመነጨውን የመረጃ ሀብት ዘመናዊ ተክኖሎጂን ተጠቅሞ በማስተዳደር በማዘመንና በማሰራጨት በኩል የተሟላ መሆኑን በጋራ በመገምገም ጎደሎውን መሙላት የሚያስችል ሀሳብ ማሰባሰብ ነው” ሲሉ ገልጸዋል።
እስከአሁን ድረስ ክልሉ ግልጽ የሆነ የመረጃ አያያዝ ስርአት የሌለው መሆኑን የገለጹት የቢሮ ሀላፊው ደመቀ ቦሩ (ዶ/ር) በዚህ ምክንያት መረጃወች በተቀናጀ በተደራጀና በተማከለ ሁኔታ ተይዘው ለክልሉ ልማት በሚጠቅም አግባብ እየተመሩ እንዳልነበር ገልጸው ይህን ችግር ሊቀርፍ የሚችል ዘመናዊ የመረጃ አስተዳደር ስርአት ስትራቴጂ መንደፍና ጥቅም ላይ ማዋል አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ብለዋል።
“መረጃ ከሀብት ሁሉ በላይ ነው፥ ባግባቡ መያዝና ጥቅም ላይ መዋል አለበት” ያሉት የቢሮው ም/ ሀላፊ አቶ ጥላሁን ፈንታው የመረጃ አያያዛችን በዘመናዊ መንገድ ካልተመራ የክልላችን ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ደህንነት ማረጋገጥ አይቻልም ብለዋል።
የተዘጋጀውን የስትራቴጂ ዶክመንት በጽሁፍ ያቀረቡት የአኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ያሲን ተሾመ መረጃን የማመንጨት፥ የማከማቸትና የማሰራጨት ቴክኖሎጂ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣ መሆኑን ገልጸው በአሁኑ ጊዜ እጅግ ፈጣንና የተራቀቀ ደረጃ ላይ መድረሱን ገልጸዋል።
በመድረኩ ተሳታፊወች በኩል ዶክመንቱን ሊያዳብሩ የሚችሉ የተለያዩና ሀሳቦች ቀርበው ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን መረጃን በዘመናዊ መንገድ መያዝና ጥቅም ላይ ማዋል ልማትን ለማፋጠን ወሳኝ ጉዳይ መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል ብለዋል።
ተሳታፊዎቹ ጭምረው እንደገለጹት “ፕላንና ልማት ቢሮ ይህን ለክልሉ የመጀመሪያ የሆነውን የዘመናዊ መረጃ አስተዳደር ስርአት ስትራቴጂ አዘጋጅቶ ባለድርሻ አካላት እንዲያዳብሩት መድረክ መፍጠሩ ክልሉን የዘመባዊ መረጃ ስርአት ባለቤት ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ያሳያል” ብለዋል።
No responses yet