Categories:

የአማራ ክልል ፕላንና ልማት ቢሮ ድጋፍና ክትትል ቡድን በሶስት ቀጠናዎች ተሠማራ ፤

ግንቦት 29/2017
ፕላንና ልማት ቢሮ
++++

የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት ማጠቃለያ የፕሮጀክት እና የመደበኛ የልማትና የመልካም አስተዳደር እቅድ አፈጻጸሞችን የሚከታተልና የሚደግፍ ቡድን ከሰኔ 02/2017 ጀምሮ ስራ አንዲጀምር በሦስት ቀጠናወች አሰማራ፡፡

ለድጋፍና ክትትል ቡድኑ የስምሪት ኦረንቴሽን የሰጡት የፕላንና ልማት ቢሮ ም/ሀላፊ  አቶ ጥላሁን ወርቅነህ እንደገለጹት “የድጋፍና ክትትል ስራው ዋና አላማ በበጀት አመቱ ውስጥ ሊፈጸሙ የታቀዱ  የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች አንዲሁም የነበር እና የአዲስ የልማት ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ከፍጥነት፤ ከጥራትና ከበጀት አጠቃቀም አንጻር በምን ደረጃ ላይ አንደሚገኙ ለማየት፤ በአፈጻጸም ሂደት ችግሮች ገጥመው ከሆነም ችግሮቹን የሚፈታ ድጋፍ ለማድረግ እና ለቀጣይ ትምህር የሚሆን ግብአት ለማግኘት ነው”  ብለዋል፡፡

የድጋፍና ክትትሉ በድኑ በሶስት ክላስተር ማለትም በማእከላዊ ጎንደር ቀጣና ጎንደር ከተማን ጨምሮ፣ በደቡብ ወሎ ቀጠና ደሴንና ኮመቦልቻን ጨምሮ እንዲሁም በባህርዳር ቀጠና ሰሜን ጎጃምን ጨምሮ የተሰማራ ሲሆን ድጋፍና ክትትሉ በቼክሊስት የታገዘ አንደሚሆን በኦረንቴሽኑ ተነስቷል፡፡

የድጋፍና ከትትል ስራው ውጤታማ አንዲሆንና የታለመለትን አላማ አንዲያሳካ ቡድን መሪዎችና የቡድኑ አባላት ተገቢውን ትኩረት ሰጥተው አንዲሰሩ ም/ቢሮ ሃላፊው ጨምረው አሳስበዋል፡፡

በሶስቱም ቀጠናዎች የሚገኙ ተደጋፊ ተቋማት የድጋፍና ክትትል ቡድኑን ተቀብለው አስፈላጊውን መረጃ በማቅረብ በኩል ትብብር ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ሲሉ ም/ቢሮ ሀላፊው አሳስበዋል፡፡

ምርምር፣ ፈጠራ፣ ትጽእኖ!
“Researching, Innovating, influencing”

‎Website:-http://anrsbopd.gov.et
‎Telegram:-https://t.me/planpdb2014
‎Facebook:-https://www.facebook.com/ANRSPADB
‎YouTube channel: – https://www.youtube.com/@ANRSBOPD-2014
‎Instagram :- https://www.instagram.com/plan_and_development_bureau/
‎x-account:- https://x.com/logout
‎tiktok:- https://www.tiktok.com/@anrs_plan_and_developmen?lang=en-GB
‎gmail address:- plananddevelopmentbureau@gmail.com

ANRS Plan and Development Buearu