የአማራ ክልል ፕላን እና ልማት ቢሮ በሀያ አምስት አመቱ አሻጋሪና ዘላቂ ልማት ፍኖተ-ካርታና በአምስት አመቱ ስተራቴጂክ እቅድ ዙሪያ ስልጠና በመስጠት ላይ ነው
ሰኔ 06/2017ዓ.ም
++++
የፕላንና ልማት ቢሮ በክልሉ አሻጋሪ እድገት እና ዘላቂ ልማት ፍኖተ ካርታና ስታቴጂክ እቅድ ዙሪያ ከሰኔ 06/2017 ዓ.ም እስከ 13/2017 ዓ.ም ለክልሉ ከፍተኛ አመራሮች የሚሰጠውን ሥልጠና ዛሬ በባህር ዳር ከተማ መስጠት ጀምሯል።
“አርቆ ማየት አልቆ መሥራት” በሚል መሪ ቃል እየተሰጠ ያለው ስልጠና አመራሩ በእቅዱ ዙሪያ በቂ ግንዛቤ አንዲይዝና በአፈጻጸሙ የሚጠበቅበትን የመሪነት ሃላፊነት አንዲወጣ ማስቻል አላማው መሆኑ በመድረኩ ተጠቁሟል፡፡
የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ክቡር አረጋ ከበደ ሰልጠናውን በመክፈቻ ንግግር የከፈቱ ሲሆን የክልሉ የ25 ዓመት ፍኖተ ካርታ እና የአምስት ዓመት አሻጋሪና ዘላቂ ልማት እቅድ በክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ አስተባባሪነት ተዘጋጅቶ ያለቀ መሆኑን ገልጸው በቀጣይ ለክልል ምክር ቤት ቀርቦ ከጸደቀ በኋላ ወደ ትግበራ ለመግባት ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል።
ክቡር ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ አንደገለጹት የሥልጠና መድረኩ ከውይይት እና ንግግር በተጨማሪ በተግባርም የክልሉን ሕዝብ ከግጭት እና ከድህነት አዙሪት በማላቀቅ በእድገት ከፍታ ላይ ለማስቀመጥ ቃል ኪዳን የሚታሰርበት መድረክ ነው፡፡
“ግጭት እና ድህነት እየተመጋገቡ እና እየተፈራረቁ የሕዝባችን ችግር ኾነው ቆይተዋል” ያሉት ርእሠ መስተዳድሩ ይህ አዙሪት ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲቆረጥ በጋራ አመራርና በሙሉ ሀላፊነት በመስራት የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መቅረፍ ይጠበቃል ብለዋል፡፡
“የሀገርና ሕዝብ ዕድገት እና ልማት መጨረሻ የሌላቸው የትውልዶች ቅብብሎሽ ናቸው” ያሉት የአማራ ክልል ፕላን እና ልማት ቢሮ ኀላፊ ደመቀ ቦሩ (ዶ.ር) ይህ የረጅም ጊዜ የልማት ዕቅድ በትውልዶች መካከል የሚደረግን የማኅበረሰብ ዕድገት እና ልማት እንዲቀጥል የሚያስችል ዋነኛ ድልድይ በመሆኑ የዚህን እቅድ ተፈጻሚንት የቀጣይ ትውልድም ተቀብሎ የሚያስቀጥለው ይሆናል ብለዋል፡፡
እቅዱ ሲዘጋጅ ለአንድ ሀገር የዕድገት አቅሞች የሆኑትን ማኅበራዊ ሀብት፣ የተፈጥሮ ሃብትን፣ ቁሳዊ ሀብትና ሰብዓዊ ሀብትን ታሳቢ በማድረግ ነው ያሉት የቢሮ ሀላፊው ድመቀ ቦሩ እነዚህን አቅሞች በመጠቀም አመራሩ እቅዱን በፈጻጸም ራእዩን ማሳካት እንደሚጠበቅበት ገልጸዋል፡፡
ቢሮ ሀላፊው ጨምረው በክልሉ የሚስተዋለውን የግጭት አዙሪት በመፍታት የሕዝቡን ሰላም እና ብልጽግና ለማረጋገጥ በዕቅድ መመራት እጅግ ወሳኝ ስለመኾኑም ገልጸዋል። የአጭር እና የረዥም ጊዜ ዕቅዶችን በአግባቡ አስተሳስሮ ማዘጋጀት፤ በጋራ እና በትጋት መፈጸም ለነገ የማይባል ወሳኝ ጉዳይ ስለመኾኑም ተናግረዋል።
ምርምር፣ ፈጠራ፣ ትጽእኖ!
“Researching, Innovating, influencing”
Website:-http://anrsbopd.gov.et
Telegram:-https://t.me/planpdb2014
Facebook:-https://www.facebook.com/ANRSPADB
YouTube channel: – https://www.youtube.com/@ANRSBOPD-2014
Instagram :- https://www.instagram.com/plan_and_development_bureau/
x-account:- https://x.com/logout
tiktok:- https://www.tiktok.com/@anrs_plan_and_developmen?lang=en-GB
gmail address:- plananddevelopmentbureau@gmail.com
ANRS Plan and Development Buearu
No responses yet