እንኳን ወደ አማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕላንና ልማት ቢሮ ይፋዊ ድህረ-ገጽ በደህና መጡ!

ፕላንና ልማት ቢሮ የክልላዊ መንግሥቱን ረቂቅ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች የሚነድፍ፣ የሚያበለጽግ፣ የልማት ዕቅዶችን ለማዘጋጀት የሚረዱ የኢኮኖሚ ጥናትና ምርምሮችን የሚያካሂድ፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊ መለኪያዎችን በማዘጋጀት አፈጻጸምን የሚለካ አንዲሁም ሁሉን አቀፍ ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ እና ቴክኖሎጂያዊ የእድገት ማእቀፎችን በመቅረጽ እንዲተገበሩ በማድረግ በኩል ከፍተኛ ሚና
የሚጫዎት ተቋም ነው፡፡

በዚህ ድህረ ገጽ ክልላዊ የልማትና የመልካም አስተዳደር እቅዶችን፣ የእቀድ አፈጻጸም ሪፖርቶችን አንዲሁም የፕሮጀክቶችን እቅድና ያሉበትን የአፈጻጸም ሁኔታ በተመለከተ ወቅታቸውን የጠበቁና ተገምግመው የጸደቁ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡

በክልሉ ውስጥ የሚገኙ የአስተዳደር እርከኖችን፣ የመሰረተ ልማት ተቋማት ስርጭትን የሚያሳዩ ካርታዎችን፣ የክልሉን የተሟላ ፕሮፋይልና ለበጀት ቀመር የሚያገለግሉ መረጃዎችን በድህረ-ገጻችን ያገኛሉ፡፡

ክልላዊ ጥቅል ምርት በእድገት ምጣኔ፣ የኢኮኖሚ ዘርፎች የእሴት ጭማሬ እድገት ምጣኔ እና ከጥቅል ምርቱ ያላቸውን ድርሻ በተመለከተ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡

ማህበራዊ ደህንነት፣ የሥነ-ሕዝብ ጉዳይ፣ የአካባቢ ዘላቂነት እና ሌሎችንም ጨምሮ ከተለያዩ ዘርፎች ጋር የተያያዙ ጠቃሚ ግብዓቶችን፣ የአሰራር ህጎችን፣ ሪፖርቶችን እና መረጃዎችን ልናደርስዎ ተዘጋጅተናል፡፡

በመሆኑም ድህረ-ገጻችንን በመጎብኘት መረጃዎችን እንዲጠቀሙ እየጋበዝን በምንለቃቸው መረጃዎችና በድህረ-ገጹ ግንባታ ዙሪያ ለሚኖረዎ ማንኛውንም አስተያየት በመቀበልና ለማስተካከል ዝግጁ መሆናችንን እንገልጻለን፡፡








About us

 በአገልግሎት ፈላጊዎች መካከል ልዩነት አናደርግም፡፡  v  በግልጽነትና ተጠያቂነት መርህ እንሰራለን፡፡  v  ለደንበኞችና ለባለድርሻ አካላት ቀልጣፋ፣ ወጪ ቆጣቢና ተደራሽ የሆነ አገልግሎት እንሰጣለን፣  v  ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር እንሰራለን፡፡  v  ምን ጊዜም ለለውጥና ለአዲስ አሠራር ዝግጁ በመሆን ተግተን እንሠራለን፡፡  v  የስራ ፍቅር፣ ከበሬታና መልካም ስነ-ምግባር መለያችን ይሆናል፡፡  v  የዕለት ሥራዎችን በዕለቱ እንዲከናወኑ ማድረግ የሥራ መመሪያችን ነው፡፡

Mission

 የክልሉን ኢኮኖሚ ሳይንሳዊ በሆነ ጥበብ በረጅም ጊዜ ዕይታ መምራት፣ ክልላዊ የልማት ቅደም ተከተል በማውጣት ውስን የማስፈፀሚያ ሀብት ውጤታማ በሆኑ የልማት ሥራዎች ላይ ተመድቦ ሥራ ላይ እንዲውል ማድረግ፣ የክልሉን ህዝብ በልማት እኩል ተሳታፊና ፍትሀዊ ተጠቃሚ የሚያደርግ ፈጣን መዋቅራዊ ለውጥ ማምጣት፣ ዘላቂ ልማት ማረጋገጥ እና ድህነትን ትርጉም ባለው ደረጃ መቀነስ፡፡

Vission

 በ2022 ዓ.ም ኢኮኖሚውን በረጅም ጊዜ ዕይታ በመምራት፣ዜጎችን እኩል የልማት ተሳታፊና ፍትሀዊ ተጠቃሚ በማድረግ መሠረታዊ የኢኮኖሚ ለውጥና ዘላቂ ልማት ለማረጋገጥና ድህነትን ለመቀነስ የልህቀት ማዕከል መሆን፡፡