የፕላንና ልማት ቢሮ የተቋማትን የ1ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት መሠረት ያደረገ የዴስክ ድጋፍ አካሄደ፥
November 9, 2026
ጥቅምት 26/2019 ዓ.ም -ባህር ዳር (ፕላንና ልማት ቢሮ) – የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፕላንና ልማት ቢሮ የተቋማትን የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የፈጻጸም ሪፖርት መሠረት ያደረገ የዴስክ ድጋፍ አካሂዷል።
የዴስክ ድጋፉ የፕላንና ልማት ቢሮ ሀላፊ ክቡር ደመቀ ቦሩ (ዶ/ር)፣ ሌሎች የቢሮው አመራሮች፥ ዳይሬክተሮችና የየዘርፎቹ ባለሙያወች በተገኙበት የተካሄድር ሲሆን በጥቅል ኢኮኖሚ፣ በዘርፎችና በአቅሞች አፈጻጸም ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ የተቋማቱን የሩብ ዓመቱ አፈጻጸም ከተያዘው ዕቅድ ጋር በማነጻጸር የአፈጻጸም ደረጃውን ለመገምገም ታስቦ የተካሄደ ነው።
በድጋፉ የተቋማቱ የአፈጻጸም ሪፖርቶች ከዕቅዶቻቸው ጋር ተነጻጽረው የተገመገሙ ሲሆን፣ በቁልፍ የአፈጻጸም አመላካቾች (KPI) ዕቅድና አፈጻጸም መካከል ያለው ተያያዥነትም ተፈትሿል።
የዴስክ ድጋፉን መሠረት በማድረግ የግምገማ ግብረ መልስ ተዘጋጅቷል። በቀጣይም በሪፖርት ትንተናው የተገኙ ግኝቶችን በመጠቀም የአፈጻጸም መረጃዎችን ከተለያዩ ምንጮች በማረጋገጥና በማነጻጸር (Triangulation) የተጠናከረ ትንተና ለማካሄድ ታቅዷል። ይህም የተገኙ ግኝቶችን የበለጠ አስተማማኝና ተጨባጭ ለማድረግ ያግዛል።



