የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ባስመዘገበው አፈጻጸም በክልሉ ከሚገኙ ቢሮዎች 1ኛ በመውጣቱ ዕውቅና እና ሽልማት ተበረከተለት ፡፡
November 10, 2026
የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት በክልሉ ከሚገኙ ቢሮዎች የተሻለ አፈጻጸም በማስመዝገብ 1ኛ ደረጃ በመውጣቱ በክቡር ርዕሰ መስተዳደር አቶ አረጋ ከበደ የዋንጫ፣ የላፕቶፕ እና የእውቅና የምስክር ወረቀት ተበርክቶለታል ፡፡
ቢሮው እውቅና እና ሽልማት ያገኘው የአማራ ክልል የ2017 በጀት ዓመት የክልል ተቋማት መሪዎች ምዝና ውጤት ግምገማ እና ዕውቅና ለመስጠት ባካሄደው መድረክ ላይ ሲሆን በዚህም 3 ዘመናዊ ላፕቶፕ፣ ዋንጫ እና የምስክር ወረቀት ተሸላሚ ሆኗል።
የቢሮው አመራሮች እና የማኔጅመንት አባላትም የዋንጫ አቀባበል ያደረጉ ሲሆን የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ ደመቀ ቦሩ (ዶ/ር) “ይህ የእውቅና የዋንጫ ሽልማት የሁሉም ሰራተኞች ጥረት ዉጤት ነው” ለመላው የማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞችም “እንኳን ደስ አላችሁ” ብለዋል፡፡



