“ገዥ ሀሳብ በመያዝ፣ በትብብር እና በቅንነት ከሰራን ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ሰርተን አሳይተናል፡፡“ ደመቀ ቦሩ (ዶ/ር)
+++
መስከረም 21/2018 ዓ.ም (ፕላንና ልማት ቢሮ) የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት በክልሉ ከሚገኙ ቢሮዎች የተሻለ አፈጻጸም በማስመዝገብ 1ኛ ደረጃ በመውጣቱ ከክልሉ መንግስት የዋንጫ፣ የላፕቶፕ እና የእውቅና የምስክር ወረቀት እንደተበረከተለት ይታወሳል።
ቢሮውም የተሰጠውን የዋንጫ፣ የላፕቶፕ እና የእውቅና የምስክር ወረቀት በማስመልከት “የትጋት ፍሬ እንዲህ ናት” በሚል መሪ ቃል ሁሉም አመራሮች እና ሰራተኞች በተገኙበት በደስታ ተከብሮ ውሏል፡፡
በዝግጅቱ ላይ የተገኙት የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ ደመቀ ቦሩ (ዶ/ር) “ገዥ ሀሳብ በመያዝ፣ በትብብር እና በቅንነት ከሰራን ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ሰርተን አሳይተናል“ ያሉ ሲሆን ይህ ስኬትም የሁሉም አመራሮች እና ሰራተኞች ውጤት በመሆኑ “እንኳን ደስ አላችሁ” ብለዋል፡፡
በክልሉ መንግስት የተሰጠን ሽልማት እና እውቅና ይበልጥ በትጋት እንድንሰራ በህዝብ እና በመንግሰት የተሰጠን ትልቅ የቤት ስራ ነው ያሉት ኃላፊው መላው አመራሮችና ጠቅላላ ሰራተኞች የተሰጠንን ተግባር እና ኃላፊነት፤ የዘወትር ጥረታችንን አጠናክረን በማስቀጠል በቁርጠኝነት በመስራት ለላቀ ስኬት መዘጋጀት አለብን ሲሉም አሳስበዋል፡፡
በእለቱ የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ባለስልጣን አመራሮች እና የማኔጅመንት አባላት የተገኙ ሲሆን የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ያየህ እንደተናገሩት “ፕላንና ልማት ቢሮ በስራ ላይ የሚገጥሙ ችግሮችን በሰከነ መንገድ በመፍታት እና በቁርጠኝነት በመስራት ውጤት ማምጣት እንደሚቻል ያሳየ እና ተሞክሮ የሚወሰድበት ቢሮ ነው” ያሉ ሲሆን በቀጣይም የላቀ ስኬት ለማስመዝገብ በአንድነት እንሰራለን ብለዋል፡፡
የተሰጠን የዋንጫ፣ የላፕቶፕና የእውቅና የምስክር ወረቀት በአርቆ አሳቢ አመራሮቻችን ጥረት እና መሪነት የተገኘ ነው ያሉት የተቋሙ ሰራተኞች ሽልማቱም ትክክለኛና የሚገባን ነው በማለት ደስታቸውን ገልፀዋል፡፡
“Researching, innovating, influencing”
Website:-http://anrsbopd.gov.et
Telegram:-https://t.me/planpdb2014
YouTube channel: – https://www.youtube.com/@ANRSBOPD-2014
Instagram :- https://www.instagram.com/plan_and_development_bureau/
x-account:- https://x.com/logout
Gmail address:- plananddevelopmentbureau@gmail.com

No responses yet