Categories:

“ያለፈውን ዓመት መልካም ተግባር በማስቀጠል፤ ዕቅዳችንን በጥራትና በቅልጥፍና በማከናወን የመፈፀም አቅማችንን ከፍ ማድረግ ይገባል”

የአማራ ክልል ፕላንና ልማት ቢሮ አማካሪ

ሙሉቀን አዳነ (ዶ/ር)፤

+++

ጥቅምት 10/2018 ዓ.ም (ፕላንና ልማት ቢሮ) የአማራ ክልል ፕላንና ልማት ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም የተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች በተገኙበት ግምገማ አካሂዷል፡፡

የግምገማ መድረኩን የመሩት የአማራ ክልል ፕላንና ልማት ቢሮ አማካሪና የጽ/ቤት ዘርፍ ተወካይ ሀላፊ ሙሉቀን አዳነ (ዶ/ር) እንደገለፁት “ቢሮው በ2017 ዓ.ም ያስመዘገበውን መልካም አፈፃፀም እንደ መስፈንጠሪያ በመውሰድ ዕቅዳችንን በጥራትና በፍጥነት በማከናወን የመፈፀም አቅማችንን ከፍ ማድረግ ይገባል” ብለዋል፡፡

የእቅድ አፈፃፀሙን ያቀረቡት የፕላንና ልማት ቢሮ የዕቅድ እና በጀት ዝግጅት ክትትል እና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ቃልኪዳን መርሻነህ ሲሆኑ በሪፖርቱ ዙሪያ ሰፊና ጥልቅ ውይይቶችን በማካሄድ በሩብ አመቱ የነበሩ ድክመትና ጥንካሬዎችን መለየት ተችሏል። የቢሮው የዚሀ ሩብ አመት አፈጻጽም ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻፀርም በተሻለ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የቀረበው ሪፖርትና ግምገማ በግልጽ አመላክቷል።

በመጨረሻም የታቀዱ ተግባራት በተሻለ መንገድ መፈፀማቸውን የገለፁት ሙሉቀን አዳነ (ዶ/ር) እንደ ክልል ታቅዶ ወደ ተግባር የተገባውን የአሻጋሪ እድገት እና የዘላቂ ልማት እቅድ በክልሉ በሚገኙ ፈጻሚ ተቋማት ትኩረት ተሰጥቶት እየተተገበረ መሆኑን በየጊዜው መከተታል እና መደገፍ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡