Categories:
ማህበረሰቡን ያሳተፈ ችግር ፈች እቅድ በማቀድ የዜጎችን ተጠቃሚነት ልናረጋግጥ ይገባል።” ደመቀ ቦሩ (ዶ/ር)
+++
የካቲት 18/2018 ዓ.ም ባህር ዳር (ፕላንና ልማት ቢሮ )
የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ከዞን እስከ ወረዳ አስተዳደር እርከን ላሉ የፕላንና ልማት ቢሮ አመራሮች የተቀናጀ የማህበረሰብ አቀፍ አሳታፊ እቅድ አዘገጃጀትን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በመስጠት ላይ ነው።
በእለቱ ተገኝተው ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የቢሮው ኃላፊ ደመቀ ቦሩ (ዶ/ር ) እንደገለጹት “ማህበረሰቡን ያሳተፈ እና ችግር ፈች የልማት እቅድ በማቀድ የዜጎችን ተጠቃሚነት ልናረጋግጥ ይገባል።” ብለዋል።
የቢሮ ሃላፊው አክለው እንደገለጹት ህብረተሰቡ የአካባቢውን ችግር በመለየት እና የችግሩ መፍቻ እቅድ በማቀድ በኩል እውነተኛ ተሳትፎ እንዲያደርግ ማስቻል ከሰልጣኞች ይጠበቃል።
ቢሮው ከሄልቬታስ አትዮጵያ እና ከዩኒሴፍ ጋር በመተባበር በተቀናጀ ማህበረሰብ ተሳትፎ እቅድ ዙሪያ ብዙ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ የተናገሩት ሃላፊው
“ህብረተሰቡ በጋራ ችግሮቹ ዙሪያ እየመከረ፤ የችግሮቹ መፍቻ እቅድ እያዘጋጀ አካባቢውን እንዲያለማ ለማድረግ ምቹ ሁኔታወችን መፍጠር አለብን” በማለት ሰልጣኞችን አሳስበዋል።
ስልጠናው በበየነ መረብ /Zoom meeting/ አማካኝነት እየተሰጠ ሲሆን የዞን ፕላንና ልማት መምሪያ ሀላፊወች፥ የወረዳ ፕላንና ልማት ጽ/ቤት ሃላፊዎች እንዲሁም ቡድን መሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል። ስልጠናው በነገው እለትም የሚቀጥል ይሆናል።
‎Researching, innovating, influencing”
‎የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
‎x-account:- https://x.com/logout
‎gmail address:- plananddevelopmentbureau@gmail.com

No responses yet

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *