Categories:
“ክልላዊ እቅዳችንን በውጤታማነት በመፈጸም እድገትን እናረጋግጥ”
ክቡር ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ
ባሕር ዳር: ጥር 24/2018 ዓ.ም (ፕላንና ልማት ቢሮ) የአማራ ክልል የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ አቅራቢነት ቀርቦ በመገምገም ላይ ነው።
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ክቡር አቶ አረጋ ከበደ እንደገለጹት ክልሉ አርቆ ማየትንና አልቆ መሥራትን ታሳቢ ያደረገ የ25 ዓመት የአሻጋሪ እድገትና ዘላቂ ልማት ፍኖተ-ካርታ አዘጋጅቶ፥ የአምስት ዓመት ስትራቴጅክ እቅድ እና አመታዊ እቅድ አቅዶ ለሁለንተናዊ ብልጽግና እየሠራ ነው ብለዋል።
ክቡር ርእሰ መስተራድሩ ጨምረው እንደገለጹት “ክልሉ አሁን እየገጠሙት ባሉ ውስጣዊ ችግሮች ታጥሮ ሳይቆም ከተለመደው አሰራር በመውጣት አቅሙን አጠናክሮ በመሥራት ላይ ነው” ብለዋል።
“እቅዱን ስናዘጋጅ “አልቆ መሥራት” ብለን የተነሳነው ችግሮችን በልዩ እይታ ተመልክተን፣ አስቸጋሪ ፈተናወችን ወደ መልካም ዕድሎች በመቀየር ፥ መልካም ጅምሮቻችንን እንደመስፈንጠሪያ ተጠቅመን ግቦቻችንን በስኬት በመፈጸም ክልላዊ ብሎም አገራዊ እድገት ለማስመዝገብ ጥረት እያደረግን ነው” ብለዋል ርእሰ ነስተዳድሩ።
“ዋነኛ አላማችን ጠንክረን ሰርተን ምርትና ምርታማነትን በመሳደግ የህዝባችንን ኑሮ ማሻሻል እና ሑለንተናዊ እድገትን ማረጋግጥ ነው” ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ የክልሉን ምርታማነት በማሳደግ በሁሉም ዘርፎች እድገትን ለማስመዝገብ የጀነርነውን መልካም አፈጻጸም አጠናክረን መቀጠል አለብን ብለዋል።
የክልሉን የስድስት ወራት አፈጻጸም ያቀረቡት የፕላንና ልማት ቢሮ ሀላፊ የተከበሩ ደመቀ ቦሩ (ዶ/ር) እንደገለጹት የክልሉ የልማትና የመልካን አስተዳደር እቅድ አፈጻጸም ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በሁሉም ዘርፎች እድገት አሳይቷል ብለዋል።
ግምገማው በነገው እለትም የሚቀጥል ይሆናል።
Researching, innovating, influencing”
የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
‎x-account:- https://x.com/logout
‎gmail address:- plananddevelopmentbureau@gmail.com

No responses yet

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *