Categories:

ፕላንና ልማት ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት ተቋማዊ የአሻጋሪ እድገትና ዘላቂ ልማት ዕቅድ አፈጻጸሙን ገመገመ

+++++++

ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም – ባሕር ዳር (ፕላንና ልማት ቢሮ)

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፕላንና ልማት ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት ተቋማዊ የአሻጋሪ እድገትና ዘላቂ ልማት ዕቅድ አፈጻጸም ገምግሟል፥ የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅም አካሂዷል።

በመድረኩ የዞንና የሪጅኦፖሊታን ከተሞች ፕላንና ልማት መምሪያ ኃላፊዎች፣ እንዲሁም የቢሮው የማኔጅመንት አባላት ተሳትፈዋል።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቢሮው ኃላፊ ደመቀ ቦሩ (ዶ/ር) ባለፈው በጀት ዓመት ተቋሙን እስከ ታች ድረስ የማደራጀት፣ መዋቅራዊ አቅሙን የማጎልበት እና የማጠናከር ሰፊ ስራዎች መሥራታቸውን ገልጸው በ2019 በጀት ዓመትም ይህው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና በተለይም የወረዳ መዋቅርን የማጠናከርና የማብቃት ጠንካራ ስራዎች እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

የፕላንና ልማት ተቋማት በተቀናጀና በተናበበ መልኩ ከሠሩ ክልላዊ እድገት ማምጣት እንደሚቻልና ለሕዝቡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት እንደሚቻል የገለጹት ቢሮው ኃላፊው በ2019 በጀት ዓመት በየደረጃው የታቀደው እቅድ ባግባቡ እንዱፈጸም ተገቢውን የክትትልና ድጋፍ ስራ መሥራት በየደረጃው ካለ አመራርና ባለሙያ ይጠበቃል ሲሉ ገልጸዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ባለፈው በጀት ዓመት ቢሮው ለዞን አመራሮችና ፈጻሚዎች የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎችን በመስጠትም ሆነ ተቋማዊ አቅሙን በመገንባት ረገድ ሰፊ ሥራዎች መስራቱን ጠቅሰው በወረዳና በከተማ ደረጃ ግን በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ተሳታፊዎቹ ጨምረው እንደገለጹት በቂ የሰው ኃይልና ግብዓት በየደረጃው እንዲሟላ፣ በአዲሱ መዋቅር ምክንያት የስራ መደቦች ደረጃ በመቀነሱ ምክንያት ባለሙያዎች ተቋሙን እየለቀቁ በመሆኑ ተገቢው የደረጃ ማስተካከያ እንዲደረግ፣ ሥልጠናዎች በዙም ከመሰጠታቸው በተጨማሪ በአካል የሚሰጡበት ሁኔታ እንዲመቻች፣ በከተማ አስተዳደሮች ደረጃ የጽሕፈት ቤቶች መዋቅር እንዲፈቀድ የሚሉ ጥያቄዎችን አቅርበዋል።

የቢሮው ኃላፊ ደመቀ ቦሩ (ዶ/ር) በበኩላቸው የቀረቡትን ጥያቄዎች በየደረጃው ለመፍታት ሰፊ ጥረት እንደሚደረግ ገልጸው ያለንን አቅም ተጠቅመን በመስራት ክልሉ ያስቀመጠውን 10.2 በመቶ የእድገት ግብ ለማሳካት መረባረብ እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።

በመድረኩ በ2018 በጀት ዓመት ከፍተኛ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የዞንና የሪጅኦፖሊታን ከተማ ፕላንና ልማት መምሪያዎች የዕውቅና ምስክር ወረቀት ሽልማት ተበርክቷል።

በዚህም መሰረት በዞኖች ደረጃ ደቡብ ወሎ ዞን 1ኛ ደረጃ፣ ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ ዞን እና ምስራቅ ጎጃም ዞን 2ኛ ደረጃ፣ አዊ ብሔረሰብ ዞን አስተዳደር 3ኛ ደረጃ የወጡ ሲሆን፣ በሪጅኦፖሊታን ከተሞች ደረጃ ደብረ ማርቆስ፣ ባሕር ዳር እና ወልደያ ከተማ አስተዳደሮች ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ደረጃ በመውጣት የዕውቅና ምስክር ወረቀት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

Researching, innovating, influencing”

‎የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ቤተሰብ ይሁኑ!
‎ 👇👇👇
‎Website:-http://anrsbopd.gov.et
‎Telegram:-https://t.me/planpdb2014
‎Facebook:- https://www.facebook.com/profile.php?id=61576561109939
Whatsapp:-https://whatsapp.com/channel/0029VbDBG9SJJhzfSZK04I0u
‎YouTube channel: – https://www.youtube.com/@ANRSBOPD-2014
‎Instagram :- https://www.instagram.com/plan_and_development_bureau/
‎x-account:- https://x.com/logout
‎tiktok:- https://www.tiktok.com/@anrs_plan_and_developmen?lang=en-GB
‎gmail address:- plananddevelopmentbureau@gmail.com

No responses yet

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *