የአብክመ ሲቪል ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ኮሚሽን የክልሉን ፕላንና ልማት ቢሮን ጎበኘ!
የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ተግባራዊ እያደረገው ያለውን የኤርጎኖሚክስ ስራ የአብከመ ሲቪል ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ኮሚሽን ታህሳስ 24/2017 አ.ም በካል ተገኝቶ ጉብኝት አደረገ።
“ቢሮው እድሳቱን ተግባራዊ ሲያደርግ የስራ ክፍሎችን በኤርጎኖሚክስ አስተሳሰብ እንዲታደሱ ማድረጉ ለሰራተኛ ጤና እና ምቾት ታስቦ እየተሰራ ለመሆኑ ማሳያ ነው” የሚል አስተያየት ከጎብኝዎቹ ቀርቧል።
“ሰራተኛው አቧራ ሳይቦንበት፥ በአላስፈላጊ ቁሳቁሶች ተከቦ ሳያጨናነቅ፣ ምቹ የስራ አካባቢ ተፈጥሮለት ስራውን እንዲሰራ የኤርጎኖሚክስ ሳይንስን ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አምነንበት እየሰራን ነው” ያሉት የፕላንና ልማት ቢሮ ሀላፊ ደመቀ ቦሩ ይህ ስራ እንደጥሩ ተሞክሮ ተወስዶ በሌሎች ተቋማትም መስፋት የሚችል ነው ብለዋል

No responses yet