Categories:
የኘላን እና ልማት ቢሮ የፕሮጀክት ክትትል ድጋፍና እና ግምገማ ቡድን ከታህሳስ 20 – 21/2017 የደሴ ከተማ አስተዳደርን በግንባታ ላይ የሚገኙትን የኮሪደር ልማት፥ የወሎ ተርሸሪ ሆስፕታል፤ የፈሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ እና ደሴ ሳብብሰቴሽን ግንባታን የአካል ድጋፍ ክትትልና ግምገማም አደረገ።
የድጋፍ ክትትልና ግምገማ ቡድኑ በግንባታ ሂደቱ የተስተዋሉ ድክመትና ጥንክሬዎችን ከባለቤት፥ ከአማካሪ፣ ከተቋራጭ ጋር በመሆን በጋራ የገመገመ ሲሆን በቀጣይ ሊስተካከሉ የሚገባቸው ጉዳዮች ተለይተው እንዲስተካከሉ ስምምነት ተደርሷል።