እንኳን ወደ አማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕላንና ልማት ቢሮ  ይፋዊ ድህረ-ገጽ በደህና መጡ! ፕላንና ልማት ቢሮ የክልላዊ መንግሥቱን ረቂቅ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች የሚነድፍ፣ የሚያበለጽግ፣ የልማት ዕቅዶችን ለማዘጋጀት የሚረዱ የኢኮኖሚ ጥናትና ምርምሮችን የሚያካሂድ፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊ መለኪያዎችን በማዘጋጀት አፈጻጸምን የሚለካ አንዲሁም ሁሉን አቀፍ ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ እና ቴክኖሎጂያዊ የእድገት ማእቀፎችን በመቅረጽ እንዲተገበሩ በማድረግ በኩል ከፍተኛ ሚና የሚጫዎት ተቋም ነው፡፡ በዚህ ድህረ ገጽ ክልላዊ የልማትና የመልካም አስተዳደር እቅዶችን፣ የእቀድ አፈጻጸም ሪፖርቶችን አንዲሁም የፕሮጀክቶችን እቅድና ያሉበትን የአፈጻጸም ሁኔታ በተመለከተ ወቅታቸውን የጠበቁና ተገምግመው የጸደቁ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ በክልሉ ውስጥ የሚገኙ የአስተዳደር እርከኖችን፣ የመሰረተ ልማት ተቋማት ስርጭትን የሚያሳዩ ካርታዎችን፣ የክልሉን የተሟላ ፕሮፋይልና ለበጀት ቀመር የሚያገለግሉ መረጃዎችን በድህረ-ገጻችን  ያገኛሉ፡፡ ክልላዊ ጥቅል ምርት በእድገት ምጣኔ፣ የኢኮኖሚ ዘርፎች የእሴት ጭማሬ እድገት ምጣኔ እና ከጥቅል ምርቱ ያላቸውን ድርሻ በተመለከተ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ ማህበራዊ ደህንነት፣ የሥነ-ሕዝብ ጉዳይ፣ የአካባቢ ዘላቂነት እና ሌሎችንም ጨምሮ ከተለያዩ ዘርፎች ጋር የተያያዙ ጠቃሚ ግብዓቶችን፣ የአሰራር ህጎችን፣ ሪፖርቶችን እና መረጃዎችን  ልናደርስዎ ተዘጋጅተናል፡፡ በመሆኑም ድህረ-ገጻችንን በመጎብኘት መረጃዎችን እንዲጠቀሙ እየጋበዝን በምንለቃቸው መረጃዎችና በድህረ-ገጹ ግንባታ ዙሪያ ለሚኖረዎ ማንኛውንም አስተያየት በመቀበልና ለማስተካከል ዝግጁ መሆናችንን እንገልጻለን፡፡
About us
  በአገልግሎት ፈላጊዎች መካከል ልዩነት አናደርግም፡፡ v  በግልጽነትና ተጠያቂነት መርህ እንሰራለን፡፡ v  ለደንበኞችና ለባለድርሻ አካላት ቀልጣፋ፣ ወጪ ቆጣቢና ተደራሽ የሆነ አገልግሎት እንሰጣለን፣ v  ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር እንሰራለን፡፡ v  ምን ጊዜም ለለውጥና ለአዲስ አሠራር ዝግጁ በመሆን ተግተን እንሠራለን፡፡ v  የስራ ፍቅር፣ ከበሬታና መልካም ስነ-ምግባር መለያችን ይሆናል፡፡ v  የዕለት ሥራዎችን በዕለቱ እንዲከናወኑ ማድረግ የሥራ መመሪያችን ነው፡፡
Mission
የክልሉን ኢኮኖሚ ሳይንሳዊ በሆነ ጥበብ በረጅም ጊዜ ዕይታ መምራት፣ ክልላዊ የልማት ቅደም ተከተል በማውጣት ውስን የማስፈፀሚያ ሀብት ውጤታማ በሆኑ የልማት ሥራዎች ላይ ተመድቦ ሥራ ላይ እንዲውል ማድረግ፣ የክልሉን ህዝብ በልማት እኩል ተሳታፊና ፍትሀዊ ተጠቃሚ የሚያደርግ ፈጣን መዋቅራዊ ለውጥ ማምጣት፣ ዘላቂ ልማት ማረጋገጥ እና ድህነትን ትርጉም ባለው ደረጃ መቀነስ፡፡
Vission
በ2022 ዓ.ም ኢኮኖሚውን በረጅም ጊዜ ዕይታ በመምራት፣ዜጎችን እኩል የልማት ተሳታፊና ፍትሀዊ ተጠቃሚ በማድረግ መሠረታዊ የኢኮኖሚ ለውጥና ዘላቂ ልማት ለማረጋገጥና ድህነትን ለመቀነስ የልህቀት ማዕከል መሆን፡፡
 Our Area of Work
What We Do
Policy Analysis and Guidance
ANRS Plan & Development Bureau Planning and Development conducts policy analysis and provides guidance on various aspects of development, including economic development, social development, demographic development, spatial development, environmental development, and institutional development. Through comprehensive research and analysis, the Bureau formulates policies to promote sustainable and inclusive development.
Evaluation and Monitoring
ANRS Plan & Development Bureau conducts periodic evaluations and monitoring of development plans to assess their progress and effectiveness. Through rigorous analysis and assessment, the Bureau identifies areas of improvement, evaluates the impact of development interventions, and makes recommendations for future planning and implementation.
News
የኘላን እና ልማት ቢሮ የፕሮጀክት ክትትል ድጋፍና እና ግምገማ ቡድን ከታህሳስ 20 – 21/2017 የደሴ ከተማ አስተዳደርን በግንባታ ላይ የሚገኙትን የኮሪደር ልማት፥ የወሎ ተርሸሪ ሆስፕታል፤ የፈሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ እና ደሴ ሳብብሰቴሽን ግንባታን የአካል ድጋፍ ክትትልና ግምገማም አደረገ። የድጋፍ ክትትልና ግምገማ ቡድኑ በግንባታ ሂደቱ የተስተዋሉ ድክመትና ጥንክሬዎችን […]
የአብክመ ሲቪል ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ኮሚሽን የክልሉን ፕላንና ልማት ቢሮን ጎበኘ! የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ተግባራዊ እያደረገው ያለውን የኤርጎኖሚክስ ስራ የአብከመ ሲቪል ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ኮሚሽን ታህሳስ 24/2017 አ.ም በካል ተገኝቶ ጉብኝት አደረገ። “ቢሮው እድሳቱን ተግባራዊ ሲያደርግ የስራ ክፍሎችን በኤርጎኖሚክስ አስተሳሰብ እንዲታደሱ ማድረጉ ለሰራተኛ […]
የአማራ ክልል ፕላንና ልማት ቢሮ የክልሉን የ2017 በጀት አመት የግማሽ አመት የልማትና የመልካም አስተዳደር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ከቢሮዎችና ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመሆን ገመገመ፡፡ ጥር 20/2017ዓ.ም የአማራ ክልል ፕላንና ልማት ቢሮ የክልሉን የ2017 በጀት አመት የግማሽ አመት የልማትና የመልካም አስተዳደር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ከቢሮዎችና ከተጠሪ ተቋማት ጋር […]

                  Top Management

Dr.Demeke Boru

Bureau Head

 Mr. Tilahun  Workineh

  Deputy Bureau Head

Mr. Tilahun Fentaw

 Deputy Bureau Head

Mr.Moges Ayanaw

Head of Public Relations

Dr. Muluken

Advisor

contact information

write us or contact us on our social media