የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ አመራሮች እና ሠራተኞች ለቀድሞው የፕላንና ልማት ቢሮ ም/ ቢሮ ኃላፊ አሸኛኘት፥ ለአዲስ ም/ቢሮ ሃላፊ አቀባበል አደረጉ ።
+++
ታህሳስ 18/2018 ዓ.ም – ባህር ዳር – (ፕላንና ልማት ቢሮ) የአብክመ ፕላንና ልማት ም/ቢሮ ኃላፊ የነበሩት ለአቶ ጥላሁን ወርቅነህ ከጥቅምት ወር 2018 አ.ም ጀምሮ በቢሮ ሀላፊነት ተሹመው ወደ ክልሉ ትምህርት ቢሮ የሄዱ ሲሆን የፕላንና ልማት አመራሮች እና ሠራተኞች አሸኛኘት አድርገውላቸዋል።
አቶ ጥላሁን ወርቅነህ በም/ቢሮ ሀላፊነት በሰሩባቸው ጊዜ የፕላንና ልማት ቢሮን ርእይ እና ተልእኮ ለማሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረጉ ፥ የተረጋጋ ባህሪ ያላቸው፣ ስራቸውን በዝምታ የሚሰሩ እና ውጤታማነት መለኪያቸው የሆነ ድንቅ መሪ፤ ከቢሮው ሰራተኞች ጋር መልካም ተግባቦት የነበራቸው ትሁት እና ቀና አመራር እንደነበሩ የቢሮ ሀላፊው ደመቀ ቦሩ (ዶ/ር) በንግግራቸው ገልጸዋል፥
ቢሮ ሀላፊው ጨምረው እንደገለጹት “አሁን በተመደቡበትን የትምህርት ቢሮ ሀላፊነት ስራ በውጤታማነት እንደሚፈጽሙና በዘርፉ የክልሉን ርእይ እንደሚያሳኩ እርግጠኛ ነኝ” ብለዋል። በቀጣም የተጣለባቸውን የመንግስትና የህዝብ ሀላፊነት በስኬት እንዲፈጽሙ መልካም ምኞታቸውንም ገልጸዋል።
የፕላንና ልማት ቢሮ አመራርና ሰራተኛ የጋራ ውጤት የሆነው የ2017 ዓ.ም ውጤታማ አፈጻጸም በቀጣይም ከትም/ቢሮ ጋር ሆነን በመረዳዳት የምናሰፋው ይሆናል ሲሉ ቢሮ ሀላፊው ጨምረው ገልጸዋል።
በፕላንና ልማት ቢሮ በነበራቸው የአመራርነት ወቅት ከሌሎች አመራሮች እና ሰራተኞች ጋር በነበራቸው ግንኙነት ደስተኛ እና ውጤታማ እንደነበሩ የገለፁት የቀድሞው ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥላሁን ወርቀነህ አሁን በተመደቡበት የኃላፊነት ቦታም የተሻለ ስራ ለመስራት እና ክልላዊ ርእዩን ለማሳካት ጥረት እንደሚያደርጉ በንግግራቸው ገልጸው አመራሩና ሰራተኛው ስላደረገላቸው አሸኛኘት ምስጋና አቅርበዋል።
የፕላንና ልማት ቢሮ ም/ ኃላፊ ሁነው በክቡር ርእሰ መስተዳድሩ ተሹመው ስራ የጀመሩትን ለዓለም ጥላሁንንም (ዶ/ር) አመራሩና ሰራተኛው አቀባበል አድርጎላቸዋል፥ በቢሮው የሚኖራቸው የስራ ቆይታም የክልሉን ርእይና ተልእኮ የሚያሳኩበት ውጤታማ የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው ተመኝቶላቸዋል።
ለአለም ጥላሁን ዶ/ር በበኩላቸው “ቢሮው ያዳበረውን ስራን በጥንካሬ የመፈፀም ልምድ ለማስቀጠል በቁርጠኝነት እንደሚጥሩና ከቢሮው አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር በቅንጅት ተናበው እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል፡፡
Researching, innovating, influencing”
Website:-http://anrsbopd.gov.et
Telegram:-https://t.me/planpdb2014
YouTube channel: – https://www.youtube.com/@ANRSBOPD-2014
Instagram :- https://www.instagram.com/plan_and_development_bureau/
x-account:- https://x.com/logout
gmail address:- plananddevelopmentbureau@gmail.com

No responses yet