ሰራተኛው በሶሻል ሚዲያ ምንነትና አጠቃቀም ዙሪያ ያለውን ግንዛቤ ለማሳደግ ያለመ ስልጠና ተሰጠ።
++++
ታህሳስ 20/2018 ዓ.ም – ባህር ዳር – (ፕላንና ልማት ቢሮ) የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት የማህበራዊ ሚዲያ ምንነት፣ አጠቃቀም እና አስፈላጊነት ዙሪያ ለቢሮው አመራሮች እና ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡
ስልጠናው የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ በሆኑት በአቶ አይለቅበት ገነት ተዘጋጅቶ የቀረበ ሲሆን በሰልጠናው ተቋማዊ ክልላዊ አገራዊና አለማቀፋዊ የሶሻል ሚዲያ አጠቃቀም ሁኔታወችን የሚያሳዩ ወቅታዊ መረጃወች ተጠናቅረው ቀርበዋል።
ሶሻል ሚዲያው በአገርም ሆነ በግለሰብ ደረጃ እያስከተላቸው ያለውን በጎ እና ጎጂ ማህበራዊ፥ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ተፅዕኖዎች በመገንዘብ፥ በጎውን በሚያሳድግ ጎጅውን በሚያስወግድ መንገድ መጠቀም እንደሚያስፈልግ በስልጠናው ተጠቁሟል።
ከትውልዱ የሥልጣኔ እድገት ጋር ተያይዘው ከመጡት የተለያዩ የቴክኖሎጂ ውጤቶች አንዱ የሆነው የማህበራዊ ሚዲያ ዘመኑ የሰጠንን ትልቅ እድል በመሆኑ ለእድገትና ለሰላም ግንባታ ስራችን ማሳለጫነት መጠቀም እንደሚገባ በሰልጠናው ተገልጿል።
ሶሻል ሚዲያው የሰው ልጅ መረጃን ለማግኘትም ሆነ በዓለም ዙሪያ ግንኙነትን ለመፍጠር የሚያደርገውን ጥረት ቀላልና ፈጣን ያደረገ ገጸ በረከት ቢሆንም ቀላል የማይባል ማህበራዊ ቀውሶችንም እያስከተለ በመሆኑ በጥንቃቄ መጠቀም እንድሚያስፈልግ ሰልጣኞች አንስተዋል።
በማጠቃለያም የሁላችንም የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም በእውቀትና በማስተዋል ላይ የተመሰረተ፥ አገርን ወደ ልማት ሰላምና ጸጥታን ወደ መረጋጋት የሚያመጣ መሆን እንዳለበት ግንዛቤ ተይዟል።
Researching, innovating, influencing”
‎x-account:- https://x.com/logout
‎gmail address:- plananddevelopmentbureau@gmail.com