ሰራተኞች ራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ከኤች አይ ቪ ኤድስ መጠበቅ እንዲችሉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።
++++
ታህሳስ 19/2018-ባህርዳር – (ፕላንና ልማት ቢሮ) የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ሰራተኛው እራሱን እና ቤተሰቡን ከኤች አይ ቪ ኤድስ መጠበቅ የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።
የስለጠና መድረኩን በንግግር የከፈቱት የፕላንና ልማት ቢሮ ሀላፊ ደመቀ ቦሩ (ዶ/ር) በንግግራቸው እንደገለጹት “የቢሮአችንም ሆነ የክልላችን እቅዶች ተፈጻሚነት የሚኖራቸው፥ የቢሮአችንም ሆነ የክልላችን ርእይ እና ተልእኮ ሊሳኩ የሚችሉት የሰው ሀይላችን ጤንነት ሲጠበቅ በመሆኑ በኤች አይ ቪ ኤድስ ዙሪያ ያለንን ግንዛቤ በማሳደግ ራሳችንንና ቤተሰባችንን ከቫይረሱ መጠበቅ አለብን” ብለዋል።
“ኤች አይ ቪ/ ኤድስ እያደረሰው ያለው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጽእኖ አሁንም ከፍተኛ ደረጃ ላይ ያለ ቢሆንም በአሁኑ ጊዜ በህብረተሰቡ ዘንድ እየተሰጠው ያለው ትኩረት ግን በጣም አናሳ እየሆነ መጥቷል” ያሉት ቢሮ ሀላፊው ሰራተኛው ይህን ችግር ችላ ሊለው አይገባም ብለዋል።
ስለጠናውን የሰጡት የክልሉ ጤና ቢሮ
የኤች አይ ቪ/ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ዕቅድ ክትትል ባለሞያ የሆኑት አቶ መልካሙ ዳኛው ሲሆኑ ኤች አይ ቪ /ኤድስ በክልላችን ከፍተኛ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እያሳደረ ያለ ችገር በመሆኑ አሁንም ትኩረት ሰጥተን ራሳችንን እና ማህበረሰቡን ልንጠብቅ ይገባል ብለዋል።
ባለሙያው ጨምረው እንደገለጹት “በክልላችን ያለው የቫይረሱ ስርጭት እሁንም እየሰፋ ያለና በሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ደረጃ እየተስተዋለ በመሆኑ ሁሉም ሰው ግንዛቤ ኖሮት ራሱንና ቤተሰቡን መጠበቅ አለበት ብለዋል።
ስልጠናውን የወሰዱት የቢሮው ሰራተኞች በበኩላቸው የተፈጠረላቸው ግንዛቤ ወቅታዊና በመረጃ ላይ የተደገፈ በመሆኑ ግንዛቤአቸውን በማሳደግ ረገድ በጣም ጠቃሚ ሆኖ እንዳገኙት ገልጸዋል።
Researching, innovating, influencing”
Website:-http://anrsbopd.gov.et
Telegram:-https://t.me/planpdb2014
YouTube channel: – https://www.youtube.com/@ANRSBOPD-2014
Instagram :- https://www.instagram.com/plan_and_development_bureau/
x-account:- https://x.com/logout
gmail address:- plananddevelopmentbureau@gmail.com

No responses yet