“ዘመናዊ የመረጃ ሥርዓትን በመዘርጋት ወጥነት ያለው እና ወቅቱን የጠበቀ የሪፖርት እና የመረጃ ልውውጥ እንዲኖር በትኩረት እየተሰራ ይገኛል፡፡” የአማራ ክልል ፕላንና ልማት ቢሮ አማካሪ ሙሉቀን አዳነ (ዶ/ር)
+++
ጥቅምት 20/2018 ዓ/ም (ፕላንና ልማት ቢሮ) የአማራ ክልል ፕላንና ልማት ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም የዞን እና የሪጆ ፖሊታን ከተማ የፕላንና ልማት ቡድን መሪዎች ጋር በበየነ መረብ (zoom meeting) አማካኝነት ግምገማ አካሂዷል፡፡
ግምገማውን በበየነ መረብ (zoom meeting) የመሩት የአማራ ክልል ፕላንና ልማት ቢሮ አማካሪ እና ተወካይ የጽ/ቤት ዘርፍ ኃላፊ ሙሉቀን አዳነ (ዶ/ር) እንደገለፁት ዘመናዊ የመረጃ ሥርዓትን በመዘርጋት ወጥነት ያለው እና ወቅቱን የጠበቀ የሪፖርት እና የመረጃ ልውውጥ እንዲኖር በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
የቢሮው የዕቅድ እና በጀት ዝግጅት ክትትል እና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ቃልኪዳን መርሻነህ የቢሮውን፣ የዞን እና የሪጆ ፖሊታን ከተማ የፕላንና ልማት ቡድን መሪዎችን የእቅድ አፈፃፀም እና አጠቃላይ ግብረመልስ ያቀረቡ ሲሆን በሩብ አመቱ የነበሩ ጥንካሬዎች እና ድክመቶች ተለይተው ውይይት ተደርጓባቸዋል፡፡
የቢሮው ዋና አማካሪ እና ተወካይ የጽ/ቤት ዘርፍ ኃላፊ ሙሉቀን አዳነ (ዶ/ር) በውይይቱ ማጠቃለያ እንደገለፁት የቢሮዎች ወጥነት ያለው የተቋማት ምዘና እና የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ ሥርዓት (Master Reporting System) እንዲኖር ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ዘመናዊ ሶፍትዌር ለምቶ ወደ ተግባር ተገብቷል ያሉ ሲሆን በቀጣይም በዞኖች ፣ በሪጆ ፖሊታን ከተሞች እና በከተማ አስተዳደሮች ሶፍትዌሩን እንዲጠቀሙ ለማድረግ በሂደት ላይ እንገኛለን ብለዋል፡፡
በዚህ ሩብ ዓመት ያልተፈፀሙ ተግባራት ተለይተው በቀጣይ ሩብ ዓመት መፈፀም እንዳለባቸው ያሳሰቡት ዶ/ር ሙሉቀን በየዞኖች እና በሪጆ ፖሊታን ከተማ የፕላንና ልማት ቡድኖች ላይ ያለውን የሰው ሃይል እጥረት እና ተያያዥ ችግሮች የቢሮው መዋቅር ፀድቆ ወደ ተግባር ሲገባ ምላሽ የሚያገኙ ችግሮች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
“Researching, innovating, influencing”
Website:-http://anrsbopd.gov.et
Telegram:-https://t.me/planpdb2014
Facebook:- https://www.facebook.com/profile.php?id=61576561109939
YouTube channel: – https://www.youtube.com/@ANRSBOPD-2014
Instagram :- https://www.instagram.com/plan_and_development_bureau/
x-account:- https://x.com/logout
tiktok:- https://www.tiktok.com/@anrs_plan_and_developmen?lang=en-GB
gmail address:- plananddevelopmentbureau@gmail.com

No responses yet