Categories:

የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕላንና ልማት ቢሮ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕላንና ልማት ቢሮ ባህርዳር በመገኘት የልምድ ልውውጥ አደረገ፡፡

+++

ጥቅምት 21/2018 ዓ.ም (ፕላንና ልማት ቢሮ)

የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕላንና ልማት ቢሮ የዳይሪክቶሮች ቡድን ባህርዳር በሚገኘው የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕላንና ልማት ቢሮ በመገኘት የልምድ ልውውጥ አድርጓል፡፡

የልምድ ልውውጥ ቡድኑ አላማ በአማራ ክልል ፕላንና ልማት ቢሮ እየተተገበረ ያለውን የማክሮ ፕላን ዝግጅት፥ የልማት እቅድ አፈጻጸም ድጋፍ ክትትልና ምዘና ስራወች እንዴት እየተተገበሩ ነው የሚለውን በአካልና በመድረክ በማየት ተሞክሮውን ወደ አፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕላንና ልማት ቢሮ ወስዶ በመተግበር አፈጻጸምን ማሳደግ የሚያስችል ስርአት መዘርጋት መሆኑን ቡድኑ ገልጿል።

የፕላንና ልማት ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥላሁን ፈንታው ቡድኑን ተቀብለው የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር አድርገዋል። አቶ ጥላሁ በንግግራቸው “የአፋር ወንድሞቻችን እንኳን ወደ አማራ ክልል በሰላም መጣችሁ። የመጣችሁት ወደራሳችሁ ክልል ነው። በቆይታችሁ ሰላምና ደስታ ተሰምቷችሁ፥ የምትፈልጉትን ተሞክሮ አግኝታችሁ እንድትመለሱ የምንችለውን እናደርጋለን ” ብለዋል።

ም/ቢሮ ሀላፊው ጨምረው እንደገለጹት “የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ በ2017 በጀት አመት በክልሉ ከሚገኙ ቢሮዎች ጋር ተወዳድሮ 1ኛ በመውጣት የዋንጫ ተሸላሚ የሆነ ቢሮ በመሆኑ ቢሮውን ለተሞክሮ ልውውጥ መርጣችሁ መምጣታችሁ ትክክለኛ ውሳኔ ነው” ብለዋል።

ቡድኑ በማክሮ ፕላን ዝግጅት ፥ በፕላን ክትትል ግምገማና ምዘና፥ በስታትስቲክስ፥ በGIS, በICT, ጄኦስፓሻል ፥ በፖሊሲ እንዲሁም በፕሮጀክት እቅድ ዝግጅት አፈጻጸምና ክትትል ስራወች ዙሪያ ጠቃሚ ተሞክሮወችን ማግኘቱን ገልጿል።

የተሞክሮ ልውውጥ ቡድን አባላቱ በሁሉም ዘርፎች ያገኙት ተሞክሮ የክልላቸውን የፕላንና ልማት ስራ ወደተሻለ ደረጃ ለማሳደግ በጣም ጠቃሚ ሆኖ እንዳገኙት ግልጸው ቢሮው ባደረገላቸው አቀባበል ደስተኛ መሆናቸውን እና፥ በቀጣይም ከክልሉ ጋር የሚኖራቸውን ግንኙነት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።

“Researching, innovating, influencing”

‎Website:-http://anrsbopd.gov.et

‎Telegram:-https://t.me/planpdb2014

‎Facebook:- https://www.facebook.com/profile.php?id=61576561109939

‎YouTube channel: – https://www.youtube.com/@ANRSBOPD-2014

‎Instagram :- https://www.instagram.com/plan_and_development_bureau/

‎x-account:- https://x.com/logout

‎tiktok:- https://www.tiktok.com/@anrs_plan_and_developmen?lang=en-GB

‎gmail address:- plananddevelopmentbureau@gmail.com