የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የ2018 በጀት አመት የ1ኛ ሩብ አመት የልማትና የመልካም አስተዳደር እቅድ አፈጻጸምን ገመገመ፥
+++++
ባህር ዳር : ህዳር 19/2018 ( ፕላንና ልማት ቢሮ)
በፕላንና ልማት ቢሮ ተዘጋጅቶ በክልሉ ም/ቤት ጸድቆ በበጀት አመቱ መጀመሪያ ወደ ትግበራ የገባው ፥ የክልላዊ አሻጋሪ እድገትና ዘላቂ ልማት ስትራቴጂያዊ እቅዱ አካል የሆነው የ2018 በጀት አመት እቅድ የመጀመሪያ ሩብ አመት (ከሀምሌ 01 – መስከረም 30) አፈጻጸም በክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ሀላፊ በተከበሩ ደመቀ ቦሩ(ፒ ኤች ዲ) አቅራቢነት ቀርቦ ተገምግሟል።
የግምገማ መድረኩን የመሩት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ አረጋ ከበደ ሲሆኑ የክልል፥ የዞን፥ የከተሞች እና የወረዳ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች የመድረኩ ተሳታፊ ሆነዋል።
ሪፖርቱ አጠቃላይ የሩብ አመቱን የዘርፎች የእቅድ አፈጻጸም ከግቦች አንጻር የገመገመ ሲሆን በተለይም የክልሉን ሠላምና ደህንነት እንዲሁም የህግ የበላይነት ማረጋገጥ፤ የተቋማት የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም መገንባት፤ ክልላዊ ወጎችን ዕሴቶችን እና ባህሎችን በማዳበር በሥነ-ምግባር የታነፀ ትውልድ ማፍራት፤ ሣይንሳዊ ዕውቀትን የርትዕ ማሕበረሰብ እሴት እና የኢኮኖሚ ዕድገት መሠረት ማድረግ፤ ምርታማነትንና ቅልጥፍናን በማሳደግ ጥራት ያለው ኢኮኖሚ መገንባት የሚሉትን ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች አፈጻጸም በጥልቀት ገምግሟል።
ሪፖርቱ ክልላዊ ጥቅል ኢኮኖሚ፥ የዘርፎች ልማት፥ የልማት አቅሞችና የልማት ፋይናንስ ስራዎችን የገመገመ ሲሆን ክልላዊ የጥቅል ኢኮኖሚ እድገትን ሊያፋጥኑ የሚችሉ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ፥ በከተማና በገጠር የስራ እድል ፈጠራ ስራዎች ትኩረት ተሰጥቷቸው እየተሰሩ መሆኑን አሳይቷል። የዋጋ ንረት ምጣኔን /inflation/ በማውረድና የኑሮ ውድነትን በመቀነስ በኩልም አበረታች ስራወች በመሰራት ላይ መሆናቸውን አሳይቷል። በመጨረሻም በአፈጻጸም የተገኙ ግኝቶችን መሰረት በማድረግ በቀጣይ ቢስተካከሉ ባላቸው ጉዳዮች ዙሪያ ምክረ- ሀሳቦችን አቅርቧል።
በግምገማው ማጠቃለያ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ አረጋ ከበደ አፈጻጸማቸው በጥሩ ደረጃ ላይ የሚገኙ ተግባራትን አጠናክሮ መቀጠል እንዲሁም የአፈጻጸም ችግሮች የተስተዋሉባቸውን ስራዎች ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ግቦችን ማሳካትና ልማት ማስመዝገብ ከሁሉም አካላት ይጠበቃል ሲሉ አሳስበዋል። በቀጣይ በየደረጃው ትኩረት ተሰጥቷቸው ሊሰሩ የሚገባቸውን ተግባራት በተመለከተም ክልላዊ አቅጣጫ ሰጥተው ግምገማው ተጠናቋል።
Researching, innovating, influencing”
Website:-http://anrsbopd.gov.et
Telegram:-https://t.me/planpdb2014
Facebook:- https://www.facebook.com/profile.php?id=61576561109939
YouTube channel: – https://www.youtube.com/@ANRSBOPD-2014
Instagram :- https://www.instagram.com/plan_and_development_bureau/
x-account:- https://x.com/logout
tiktok:- https://www.tiktok.com/@anrs_plan_and_developmen?lang=en-GB
gmail address:- plananddevelopmentbureau@gmail.com

No responses yet