ፕላንና ልማት ቢሮ በለሙ ሶፍተዌሮች አጠቃቀም ዙሪያ ለርእሰ መስተዳድሩ አማካሪዎች ስልጠና ሠጠ
+++
ሕዳር 23/2018 ዓ.ም – ባህር ዳር – (ፕላንና ልማት ቢሮ)
የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ በአዋጅ ቁጥር 300/2017 የተሰጠውን የልማት ዕቅድ ፕሮግራም እና ፕሮጀክቶች አዘገጃጀት፤ የክልሉን ተቋማት የአጭር፣ የመካከለኛ እና የረዥም ጊዜ ዕቅድ አተገባበር ውጤታማነት በኃላፊነት የመከታተል፣ የመገምገም፣ እና የተግባር አፈፃፀምን መሠረት አድርጎ ተቋማትን የመመዘን ተግባርና ሀላፊነት በውጤታማነት ለመከወን የሚያስችሉትን የተለያዩ ሶፍትዌሮች በማልማት እና ወደ ስራ በማስገባት ላይ ሲሆን በለሙ ሶፍትዌሮች አጠቃቀም ዙሪያ ተከታታይ ስልጠናዎችን በመስጠት ላይ ነው፡፡
በዚህም መሠረት ከክልሉ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ጋር በመተባበር በቅርቡ አልምቶ ወደ ስራ ባስገባቸው የፕሮጀክት ማኔጅመንት አስተዳደር /Project Management system/ እና የተቋማት የአፈፃፀም ምዘና (KPI) ሶፍትዌሮች ዙሪያ ለክልሉ ርእሰ መስተዳድር አማካሪዎች ስልጠና ሰጥቷል፡፡
ስልጠናውን በንግግር ያስጀመሩት የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ሀላፊ ደመቀ ቦሩ (PhD) በንግግራቸው “የስልጠናው አላማ አማካሪዎች የሶፍዌሩን አጠቃቀም ተረድተው የክልሉን የእቅድ አፈጻጸም መረጃ እንዲያገኙና የእቅድ አፈጻጸሙን እንዲደግፉ ከማስቻሉም በተጨማሪ በወቅታዊ መረጃ ላይ ተመሥርተው የማማከር ተግባርና ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ማስቻል ነው” በማለት ተናግረዋል፡፡
የቢሮ ሀላፊው ጨምረው እንደገለጹት “ቢሮው ከተለመዱ የማኑዋል አሰራሮች ለመውጣትና ቴክኖሎጂ መር አሰራሮችን ተከትሎ ቀልጣፋና ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት ጥረት እያረገ ነው” ብለዋል፡፡
የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው “የተሰጠን ስልጠና ሶፍተዌሮቹን በመጠቀም የክልሉን የልማት አፈጻጸም እንድንከታተል የሚያስችለን ነው” ያሉ ሲሆን “ኮምፒውተራችንንም ሆነ ተንቀሻቃሽ ስልካችንን ተጠቅመን በክልሉ እየተሰሩ ያሉ ፕሮጀክቶች እና ሌሎች የልማት ስራዎች ያሉበትን ወቅታዊ ሁኔታ ተረድተን የማማከር ተግባርና ሀላፊነታችንን እንድንወጣ የሚያስችለን አቅም ነው” በማለት ገልጸዋል፡፡
ሰልጣኞቹ ጨምረው እንደገለፁት “ቢሮው እያለማው የሚገኘው ሶፍተዌር አሰራራችን ከዘልማዳዊ አሰራር የወጣ እና ቴክኖሎጂ መር እንዲሆን በማድረግ ክልሉ ያስቀመጠውን የ25 ዓመት የአሻጋሪ እድገትና ዘላቂ ልማት እቅድ ለማስተግበር የሚያስችል በመሆኑ ሌሎች ተቋሞች ተሞክሮ መውሰድ ይገባቸዋል” ብለዋል፡፡
Researching, innovating, influencing”
Website:-http://anrsbopd.gov.et
Telegram:-https://t.me/planpdb2014
Facebook:- https://www.facebook.com/profile.php?id=61576561109939
YouTube channel: – https://www.youtube.com/@ANRSBOPD-2014
Instagram :- https://www.instagram.com/plan_and_development_bureau/
x-account:- https://x.com/logout
tiktok:- https://www.tiktok.com/@anrs_plan_and_developmen?lang=en-GB
gmail address:- plananddevelopmentbureau@gmail.com

No responses yet