ፕላንና ልማት ቢሮ ክልሉ በተባበሩት መንግስታት ህጻናት አድን ድርጅት /ዩኒሴፍ/ ድጋፍ ተግባራዊ እያደረገው ባለው ፕሮግራም ዙሪያ ከዩኒሲፍ ከመጡ አመራሮች ጋር ውይይት አካሄደ፡፡
+++
ህዳር 27/2018 ዓ.ም – ባህር ዳር – (ፕላንና ልማት ቢሮ)
የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕላንና ልማት ቢሮ ክልሉ በተባበሩት መንግስታት የህፃናት አድን ድርጅት (ዩኒሴፍ) ድጋፍ በሰሜን ጎጃም ዞን ባህር ዳር ዙሪያ ወረዳ ተግባራዊ እያደረገው ባለው የሶሻል ፖሊሲ እና የህጻናት ተጠቃሚነት ፕሮግራም አፈጻጸም ዙሪያ ከዩኒሴፍ የመጡ የስራ ሃላፊወች ጋር ውይይት አካሂዷዋል።
በውይይቱ የፕላንና ልማት ቢሮ አመራሮች የማክሮ ፕላን ተወካይ ዳይሬክተርና ባለሙያዎች ፤ በዩኒሴፍ የማህበራዊ አማካሪ (Chief adviser) ሚስተር ዳንዔል ኩመቲዝ፤ country office and Amhara field office አስተባባሪዎች የተገኙ ሲሆን በፕሮግራሙ መሰረት እየተሰሩ ባሉ ስራዎች እና በቀጣይ ተግባራት ዙሪያ ውይይት ተደርጓል፡፡
በውይይቱ የፕላንና ልማት ቢሮ አማካሪ ሙሉቀን አዳነ (ዶ/ር) እንደገለጹት ክልሉ በዩኒሴፍ ድጋፍ ተግባራዊ እያደረገው የሚገኘው በሶሻል ፖሊሲ ፕሮግራም/social policy progeramme/ የpublic finance for children /PF4C/ ተግባር ሲሆን የህጻናት እኩልነት እና ፍትሃዊ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እንዲቻል ተቋማት በቂ ትኩረት ሰጥተው አቅደው እንዲፈጽሙ በማድረግ በኩል ፕላንና ልማት ቢሮ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፥ ተቋማቱም አበራታች ውጤቶችን እያስመዘገቡ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በዩኒሴፍ የማህበራዊ አማካሪ ሚስተር ዳንዔል ኩመቲዝ፤ እና ከcountry office እንዲሁም ከAmhara field office አስተባባሪዎች በበኩላቸው እንደገለጹት ፕላንና ልማት ቢሮ ከዩኒሴፍ ጋር በመሆን ተግባራዊ እያደረገው ያለውን ፕሮግራሞ አቅዶ በመፈጸም በኩል በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝና ሌሎች ክልሎች ተሞክሮ ሊወስዱበት የሚችሉ መሆኑን አንስተዋል፡፡
በክልሉ ተግባራዊ እየተደረገ ያለው ጥናት ወደ ሌሎች ወረዳወችም በማስፋት የህጻናት ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ስራው ተደራሽ መሆን የሚቻልበት ሁኔታ ቢመቻች የሚል ሀሳብ በውይይቱ ተነስቷል፡፡
ፕሮግራሙን በውጤታማነት ተግባራዊ በማድረግ ሂደት ክልሉን እያጋጠሙት ባሉ ችግሮች/ bottlenecks/ ዙሪያ ውይይት የተደረገ ሲሆን የበጀት እጥረት ዋነኛ ማነቆ እንደሆነ በውይይቱ ተጠቁሟል፥ ተጨማሪም ቴክኒካዊና ሙያዊ የአቅም ግንባታ ስልጠናወች እንደሚያስፈልጉም ተነስቷል።
ከዩኒሴፍ የመጡ አመራርች እንደገለጹት ክልሉ እስካሁን ያለው አፈጻጸም ጥሩ በመሆኑ እያጋጠሙት ያሉትን ችግሮች በቀጣይ ለመፍታትና የበለጠ ውጤታም እንዲሆን ለማስቻል በቴክኒክ እና በገንዘብ የሚያደርገውን እገዛ ለማጠናከር ጥረት ይደረጋል ብለዋል።
Researching, innovating, influencing”
Website:-http://anrsbopd.gov.et
Telegram:-https://t.me/planpdb2014
Facebook:- https://www.facebook.com/profile.php?id=61576561109939
YouTube channel: – https://www.youtube.com/@ANRSBOPD-2014
Instagram :- https://www.instagram.com/plan_and_development_bureau/
x-account:- https://x.com/logout
tiktok:- https://www.tiktok.com/@anrs_plan_and_developmen?lang=en-GB
gmail address:- plananddevelopmentbureau@gmail.com

No responses yet