ፕላንና ልማት ቢሮ በክልሉ በሚገኙ ቢሮዎች የልማት እቅድ አፈጻጸም ክትትል እና ድጋፍ ማካሄድ ጀመረ፡፡
+++
ህዳር 29/2018 ዓ.ም – ባህር ዳር – (ፕላንና ልማት ቢሮ)
የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ በአዋጅ ቁጥር 300/2017 የተሰጠውን የልማት ዕቅድ ፕሮግራም እና ፕሮጀክቶች አዘገጃጀት፤ የክልሉን ተቋማት የአጭር፣ የመካከለኛ እና የረዥም ጊዜ ዕቅድ አተገባበር ውጤታማነት በኃላፊነት የመከታተል፣ የመገምገም፣ እና የተግባር አፈፃፀምን መሠረት አድርጎ ተቋማትን የመመዘን ተግባርና ሀላፊነት የተሰጠው ሲሆን ይህን ሀላፊነቱን ለመወጣት የ2018 በጀት አመት የ1ኛው ሩብ ዓመት የእቅድ አፈፃፀም ክትትል እና ድጋፉ ማካሄድ ጀምሯል፡፡
የደጋፍና ክትትል ቡድኑ በአራት ቡድኖች የተደራጀ ሲሆን ከዛሬ ህዳር 29/2018 ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ የስራ ቀናት የክትትልና ድጋፍ ስራውን የሚያከናውን ይሆናል ፡፡
የድጋፍ እና ክትትል ስራውን በበላይነት የሚመሩት የቢሮው ም/ኃላፊ ለዓለም ጥላሁን (ዶ/ር) እንደገለጹት እንደ ክልል የ25 ዓመት የአሻጋሪ እድገት እና የዘላቂ ልማት ፍኖተ ካርታ ፤ የአምስት ዓመት የስትራቴጂክ ዕቅድ እንዲሁም የ2018 በጀት አመት የአሻጋሪ እድገት እና የዘላቂ ልማት እቅድ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ የተገባ ሲሆን የክልሉ ተቋማት በእቅዳቸው መሰረት እየፈጸሙ መሆኑን መከታተልና መደገፍ አስፈላጊ በመሆኑ የድጋፍና ክትትል ስራው መጀመሩን ተናግረዋል፡፡
የድጋፍና ክትትል ስራው ከመጀመሩ በፊት ከቢሮዎቹ ተግባር እና ኃላፊነት እና አመታዊ እቅድ የመነጨ የድጋፍና ክትትል ቸክሊስት ተዘጋጅቶ በቢሮው ከፍተኛ አመራሮች እና የማኔጅመንት አካል ተገምግሞ ቀድሞ እንዲደርሳቸው የተደረገ መሆኑን የገለጹት ም/ቢሮ ኃላፊው ተቋማት ለክትትልና ድጋፍ የተሰማራውን ቡድን በአግባቡ በመቀበል በቼክሊስቱ መሰረት የሚጠይቀውን መረጃ በማቅረብ በኩል ትብብር እንዲያደርጉለት ጥሪ አቅርበዋል፥ የድጋፍና ክትትል ቡድኑም በእውቀት ላይ የተመሰረተ ድጋፍ እንዲያደርግ አሳስበዋል።
በዕቅድ የተቀመጡ የልማት ግቦችና ኢላማዎች በተቀናጀ፣ በተደራጀ አግባብ በመፈጸም ክልላዊ ርእያችንን በማሳካት ክልሉ የጀመረውን የብልጽግና ጉዞ ማፋጠን ይገባል ያሉት ም/ቢሮ ሀላፊው ለዚህ ስኬት የሚሆን ስራ በአቅዱ መሰረት እየተሰራ መሆኑንና ውጤት እየተነዘገበ መሆኑን መከተትልና መደገፍ ይጠበቃል ብለዋል።
በዛሪው እለት ትምህርት ቢሮ፣ ጤና ቢሮ እና እንስሣት ሀብት ልማት ቢሮ ድጋፍና ክትትል ተደርጎላቸዋል። በድጋፍና ክትትሉ በየቢሮወቹ የተፈጸሙና ያልተፈጸሙ የእቅድ ተግባራትን መለየት ተችሏል። ያልተፈጸሙት በቀጣይት ትኩረት ተሰጥቷቸው እንዲፈጸሙ ጥንቃሬወችም የበለጠ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ቡድኖቹ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
Researching, innovating, influencing”
Website:-http://anrsbopd.gov.et
Telegram:-https://t.me/planpdb2014
Facebook:- https://www.facebook.com/profile.php?id=61576561109939
YouTube channel: – https://www.youtube.com/@ANRSBOPD-2014
Instagram :- https://www.instagram.com/plan_and_development_bureau/
x-account:- https://x.com/logout
tiktok:- https://www.tiktok.com/@anrs_plan_and_developmen?lang=en-GB
gmail address:- plananddevelopmentbureau@gmail.com

No responses yet