“የድጋፍ እና ክትትል ስራው የተቋማትን የአፈጻጸም ድክመትና ጥንካሬወች ለይተን እንድናውቅ ረድቶናል”
ደመቀ ቦሩ (ዶ/ር)
+++
ታህሳስ 06/2018 ዓ.ም – ባህር ዳር – (ፕላንና ልማት ቢሮ)
የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ከህዳር 29/2018 ጀምሮ በአራት የድጋፍና ክትትል ቡድኖች ሲያካሂደው የቆየውን የድጋፍና ክትትል ስራ በያዘው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት አጠናቋል።
የድጋፍና ክትትል ስራው የተቋማትን የእቅድ አፈጻጸም ምን ያህል ለይቷል? ተቋማት እቅዶቻቸውን በመፈጸም ሂደት ምን ችግሮች ገጠሟቸው? የተቋማት አፈጻጸም ለማክሮ ኢኮኖሚው እድገት ምን ጉልህ ሚና አለው? የተቋማትን ድክመትና ጥንካሬ ለይቶ በማሳየት በኩል ድጋፍና ክትትሉ ምን ያህል ውጤታማ ነበር? በሚሉት የድጋፍና ክትትል ግምገማው ዋነኛ ጭብጦች ነበሩ።
የግምገማ መድረኩን የመሩት የፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ ደመቀ ቦሩ (ዶ/ር) ሲሆኑ የቢሮው ከፍተኛ አመራሮች፥ ዳይሬክተሮችና የድጋፍና ክትትል ቡድኑ አባል የሆኑ ባለሙያወች የመድረኩ ተሳታፊወች ነበሩ።
የድጋፍና ክትትል ስራው የተቋማትን ድክመትና ጥንካሬ በደንብ ለይቶ ያሳየ በመሆኑ ለቀጣይ ስራወቻቸው አቅም የሚፈጥርላቸው፥ በእቅዳቸው መሰረት እንዲፈጽሙ የሚያነሳሳቸውና በአሁኑ ጌዚም የአፈጻጸም ደረጃቸው የት ላይ እንደሆነ ማሳየት የቻለ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ተቋማት ከክልሉ የአሻጋሪ እድገት እና ዘላቂ ልማት ስትራቴጅክ እቅድ ላይ የተቀመጠላቸውን ግቦች መሰረት አድርገው አቅደው ወደ ስራ መግባታቸው ፣ ባላቸው በጀት እና የሰው ሃይል እቅዳቸውን ለመፈፀም ጥረት ማድረጋቸው እጅግ ተስፋ ሰጭ ቢሆንም ሩብ አመቱ በአብዛኛው የዝግጅት ምእራፍ ስራወች የሚሰሩበት በመሆኑ ለቀጣይ ሩብ አመት ስራወች የበለጠ ዝግጁ መሆን እንደሚጠበቅባቸው በመድረኩ ተገልጿል።
የድጋፍና ክትትል ስራው የተቋማትን ቴክኒካዊ ክፍተቶች በመሙላት ለበለጠ ውጤታማነት በማነሳሳት በኩል ጠቃሚ እንደነበር ተገልጿል።
Researching, innovating, influencing”
Website:-http://anrsbopd.gov.et
Telegram:-https://t.me/planpdb2014
Facebook:- https://www.facebook.com/profile.php?id=61576561109939
YouTube channel: – https://www.youtube.com/@ANRSBOPD-2014
Instagram :- https://www.instagram.com/plan_and_development_bureau/
x-account:- https://x.com/logout
tiktok:- https://www.tiktok.com/@anrs_plan_and_developmen?lang=en-GB
gmail address:- plananddevelopmentbureau@gmail.com

No responses yet