“ስነ- ህዝብ በሃገር ልማት ማዕቀፍ ውስጥ ጉልህ ድርሻ ያለው ሰፊ የልማት ማዕከል ነው”
ለዓለም ጥላሁን (ዶ/ር)
+++
ታህሳስ 17/2018 ዓ.ም – ባህር ዳር – (ፕላንና ልማት ቢሮ) የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ መንግስታዊ እና የሲቪል ማህበራት ድርጅት ተወካዮች በተገኙበት የስነ-ህዝብ እና ልማት ፎርም አካሂዷል፡፡
ፎረሙን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ለዓለም ጥላሁን (ዶ/ር) እንደተናገሩት ስነ- ህዝብ በሀገር ልማት ማዕቀፍ ውስጥ ጉልህ ድርሻ ያለው ሰፊ የልማት ማዕከል ነው ያሉ ሲሆን የህዝብ ቁጥርን ከልማት ፍላጎት እና ፍትሃዊነት ጋር የተጣጣመ እንዲሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትኩረት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል፡፡
ከፎርሙ ጋር በተያያዘ የመወያያ ሰነድ በአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ የስነ ህዝብ እና ልማት ዳይሬክተር አቶ ገለጠው እንግዳው ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን የህዝብ እድገትን ከልማት እድገት ጋር በማመጣጠን የህብረተሰቡን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል ተቋማት የስነ ህዝብ ፖሊሲውን ተግባራዊ ከማድረግ አኳያ የስነ ህዝብ መረጃ በመጠቀም በዕቅድ በማካተት ስራ ላይ መዋል እንዳለባቸው ተጠቁሟል።
ተቋማት የስነ ህዝብ እቅድ አካተው እንዲያቅዱ ፕላንና ልማት ቢሮ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ከተሳታፊዎች የተነሳ ሲሆን እንደ ሀገር የስነ ህዝብ ፖሊሲ ቢሻሻል እና የህዝብና ቤት ቆጠራ የሚደረግበት ኩነት ቢፈጠር ክልሉ ያለውን የሰው ሃብት ለማወቅና ተገቢውን የልማት ፍላጎት በመለየት የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ ያግዛል ብለዋል፡፡
በመጨረሻም ውይይቱን የመሩት የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ አማካሪ ሙሉቀን አዳነ (ዶ/ር) በበኩላቸው በክልሉ ስነ-ህዝብ ትሩፋትን እውን ለማድረግ የዕድሜ አወቃቀር ለውጥን ማፋጠንና ትሩፋቱን በማሳካት በኩል የማይተካ ሚና ባላቸው በጤና፣ በትምህርት፣ የስራ እድልና መልካም አስተዳደር ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡
Researching, innovating, influencing”
‎x-account:- https://x.com/logout
‎gmail address:- plananddevelopmentbureau@gmail.com