Categories:
የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ በደቡብ ወሎ ቀጠና ለሚገኙ ተቋማት የልማት እቅድ አፈጻጸም የክትትልና ድጋፍ ስራ በማካሄድ ላይ ነው፣
+++
ታህሳስ 24/2018 ዓ.ም – ባህርዳር- (ፕላንና ልማት ቢሮ) የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ በአዋጅ ቁጥር 300/2017 የተሰጠውን የክልሉን ተቋማት የአጭር፣ የመካከለኛ እና የረዥም ጊዜ ዕቅድ አተገባበር ውጤታማነት የመከታተል፣ የመገምገም እንዲሁም አፈፃፀምን መሠረት አድርጎ ተቋማትን የመመዘን ተግባርና ሀላፊነት ለመወጣት የ2018 በጀት አመት የ2ኛው ሩብ ዓመት የእቅድ አፈፃፀም ክትትል እና ድጋፉ ስራ በደቡብ ወሎ ቀጠና በደሴ ከተማ መመሪያዎች ተገኝቶ የድጋፍና ክትትል በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
ቢሮው ለክትትልና ድጋፍ ከመረጣቸው ቀጠናዎች መካከል ደቡብ ወሎ ቀጠና አንዱ ሲሆን በዚህ ቀጠና በቀዳሚነት የታየው የደሴ ከተማ አስተዳደር ነው :: በዚህ ከተማ አስተዳደር ለድጋፍና ክትትሉ የተመረጡ ተቋማት ለማክሮ ኢኮኖሚው ጉልህ ድርሻ ያላቸው ማለትም ግብርና፣ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት፣ ማዕድን፣ ጤና፣ ትምህርት እና ባህል ቱሪዝም እና ስፖርት መመሪያዎች ሲሆኑ በተጨማሪ አገራዊና ክልልዊ ኢንሸቲቮች ላይም የድጋፍና ክትትል ስራ ተሰርቷል።
የክትትልና ድጋፍ ስራው በመስክና በዴስክ የተካሄደ ሲሆን ተቋማት ከተሰጣቸው ተልዕኮ አንፃር በተለይም ከአሻጋሪ እድገትና ዘላቂ ልማት እቅዱ አኳያ በስድስት ወሩ እናከናውነዋለን ብለው ያቀዷቸውን ተግባራት መነሻ በማድረግ በሁሉም ተቋማት የተቋማት አመራሮችና የማኔጅመንት አባላት በተገኙበት ውይይት ውይይቶች ተካሂደው በአፈፃፀም የተስተዋሉ ጥንካሪዎችን እና ውስንነቶችን መለየት ተችሏል።
በውይይቱም ጥንካሬዎቹ የበለጠ እንዲጠነክሩ እና ዝቅተኛ አፈፃፀም የታየባቸው ተግባራት ደግሞ በቀጣይ ሩብ ዓመታት ትኩረት ተሰጥቷቸው እንዲፈፅሟቸው የሚያስችል ድጋፍ መስጠት ተችሏል።
Researching, innovating, influencing”
‎x-account:- https://x.com/logout
‎gmail address:- plananddevelopmentbureau@gmail.com