የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕላን እና ልማት ቢሮ በሰሜን ሸዋ ክላስተር ስር በሚገኙ ተቋማት የድጋፍና ክትትል ስራወችን በማካሄድ ላይ ነው።
+++
ታህሳስ 24/2018 ዓ.ም – ባህርዳር- (ፕላንና ልማት ቢሮ) የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት እቅድ አፈፃፀም የድጋፍና ክትትል ተግባር በተለያዩ የድጋፍ ቀጠናወች ማካሂዱን ቀጥሏል።
ከታህሳስ 20/2018 ዓ.ም ጀምሮ በሰሜን ሸዋ ክላስተር በደ/ብርሀን ሪጆፖሊታን ከተማ 4 ተቋማትን ማለትም ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ፣ ጤና መምሪያ፣ ትምህርት መምሪያ እና ባ/ቱ/ስፖርት መምሪያን የመከታተልና የመደገፍ ስራ ተሰቷል።
በ20/04/2018 ዓ.ም በደ/ብርሀን ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመን መምሪያ የተከናወኑ የኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም፣ የወጭ እና ስትራቴጅክ ተኪ ምርት እንዲሁም የገቢ መጠን፣ የመዋለ ንዋይ ፍሰት፣ የመሰረተ ልማት አቅርቦት፣ በማዕድን ሀብት ልማትና በዘርፉ የተፈጠሩ የስራ እድሎችን የአፈጻጸም ሁኔታ መገምገምና መደገፍ ተችሏል።
ከጤና መምሪያ ተግባራት አኳያ የእናቶችንና ህፃናትን ሞት መቀነስ፣ ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን መከላከልና መቆጣጠር ፣ በጤና ተቋማት የመድሀኒት አቅርቦትና ስርጭት፣ የጤና መሠረተ ልማት አቅርቦት፣ የጤና መድህን የስራ እንቅስቃሴዎች አፈጻጸም ምን እንደሚመስል የተቋማት ኃላፊዎችና የማኔጅመንት አባላት በተገኙበት የድጋፍና ክትትል ስራ ተሰርቷል።
በድጋፍና ክትትል ስራው የተሻለ ውጤት የተመዘገበባቸው ተግባራት ተጠናክረው እንዲቀጥሉና ውስንነት የታየባቸው ግቦች ደግም በቀጣይ ወራት ትኩረት ተሰጥቷቸው እንዲፈጸሙ የሚያስችል ድጋፍና ክትትል ማድረግ ተችሏል ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በ21/04/2018 ዓ.ም ቡድኑ የድጋፍና ክትትል ስራውን በማጠናከር በደ/ብርሀን ትምህርት መምሪያ የትምህርት ጥራትና ተደራሽነት፣ የትምህርት ቤቶች ደረጃ ማሻሻል፣ የትምህርት አመራርና ተጠያቂነትን ማረጋገጥ ፣የተማሪዎችን የማቆየትና ማሳለፍ፣ የትምህርት ፍትሀዊነትና አካታችነት፣ የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ያለበት ሁኔታ፣የተማሪ ምገባና የትምህርት ለትውልድ ኢንሸቲቮች ፣ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርትን ማጠናከር ፣ በዘርፉ የተፈጠረ የስራ እድል አፈጻጸሞች በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኙ በመስክና በዴስክ ማየትና መደገፍ ተችሏል ።
በተጨማሪም በባ/ቱ/ስፖርት ተቋም የተከናውኑ የሀገር ውጭና የሀገር ውስጥ ቱሪስት ፍሰትን ማሳደግ፣ የቱሪስት መዳረሻዎችን መለየትና ማልማት ፣ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶችን መጠበቅ፣መንከባከብና መጠገን፣ ለሆቴል ኢንዱስትሪው ድጋፍ በማድረግ ደረጃቸውን ማሳደግ ተግባራት ዙሪያ የተሰሩ ስራወችን የማየትና የመደገፍ ስራ ስራ መስራት ተችሏል።
ቡድኑ በ22/04/2018 ዓ.ም ባካሄደው የድጋፍና ክትትል ስራ የመኸር ሰብል ምርት፣ የነባርና አዲስ መስኖ ፣ የግብዓት አቅርቦት ሁኔታ ፣ ሜካናይዜሽን ፣ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራ እና የግብርና ኢንሸቲቮችን ውጤታማ ከማድረግ አኳያ በሁሉም ተቋማት በአፈፃፀም የተስተዋሉ ድክመትና ጥንካሪዎችን መለየት የቻለ ሲሆን የተቋማት አመራሮችና የማኔጅመንት አባላት በተገኙበት ውይይት ተካሂዶ ድክመቶቹ እንዲታረሙ ጥንካሬዎቹ የበለጠ እንዲጠነክሩ እና ዝቅተኛ አፈፃፀም የታየባቸው ተግባራትም ትኩረት ተስጥቷቸው በቀጣይ ሩብ ዓመት እንዲፈፅሙ የሚያስችል ድጋፍ መስጠት ችሏል።
ድጋፍና ክትትሉ በቀጣይ ቀናት በሰሜን ሽዋ ዞን ተቋማት ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።
Researching, innovating, influencing”
‎x-account:- https://x.com/logout
‎gmail address:- plananddevelopmentbureau@gmail.com