የፕላንና ልማት ቢሮ በሰሜን ሽዋ እና ደቡብ ወሎ ቀጠናወች እያካሄደው ያለውን ድጋፍና ክትትል ስራ አጠናክሮ ቀጥሏል።
+++
ታህሳስ 24/2018-ባህርዳር-(ፕላንና ልማት ቢሮ)
የፕላንና ልማት ቢሮ በሰሜን ሸዋ እና ደቡብ ወሎ ዞኖች ያሰማራቸው የድጋፍና ክትትል ቡድኖች የዞንና የከተማ አስተዳደር ተቋማትን የመደገፍና የመከታተል ስራወችን በመስራት ላይ ናቸው።
ቡድኖችን የሚመሩት የቢሮው ም/ል ሀላፊ ለአለም ጥላሁን (ዶ/ር) ሲሆኑ የድጋፍና ክትትል ስራው በታቀደው ደረጃ እየተፈጸመ መሆኑን ገልጸዋል።
የድጋፍና ክትትል ስራው አላማ የክልሉን የአሻጋሪ እድገትና ዘላቂ ልማት እቅድ መሰረት አድርጎ የተዘጋጀውን የ2018 በጀት አመት የተቋማትን የእቅድ አፈጻጸም በአካል መመልከትና ምን ያህል በስኬታማነት እየተፈጸመ ነው የሚለውን በመመልከት ድክመትና ጥንካሬወችን በመለየት ማስተካከያዎች እንዲደረጉ ማስቻል ነው ያሉት ም/ቢሮ ሀላፊው አላማውን በሚያሳካ ሁኔታ ስራወች እየተሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።
በሁለቱም ዞኖች እና በደሴ እና በደብረ ብርሃን ከተማወች የልማት ፕሮጀክቶች አፈጻጸምን በአካል በማየት ድጋፍ የተደረገ ሲሆን በድጋፍና ክትትሉ የዞንና ከተማ አስተዳደሮች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
Researching, innovating, influencing”
Website:-http://anrsbopd.gov.et
Telegram:-https://t.me/planpdb2014
YouTube channel: – https://www.youtube.com/@ANRSBOPD-2014
Instagram :- https://www.instagram.com/plan_and_development_bureau/
x-account:- https://x.com/logout
gmail address:- plananddevelopmentbureau@gmail.com

No responses yet