የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕላን እና ልማት ቢሮ በሰሜን ሸዋ ክላስተር በደ/ብርሀን ከተማ ሲያካሂደው የነበረውን የድጋፍና ክትትል ስራ የመውጫ ውይይት በማካሄድ አጠናቀቀ።
+++
ታህሳስ 27/2018-ባህርዳር-(ፕላንና ልማት ቢሮ) ፕላንና ልማት ቢሮ ከታህሳስ 20/2018 ዓ.ም ጀምሮ በሰሜን ሸዋ ክላስተር ያሰማራው የድጋፍና ክትትል ቡድን በደብረ ብርሀን ከተማ በአምስቱ ተቋማት ማለትም ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ፣ ግብርና፣ ትምህርት ፣ ጤና እና ባህልና ቱሪዝም ተ/ፅ/ቤት ተገኝቶ ሲያካሂደው የቆየውን የዴስክና የመስክ የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት እቅድ አፈፃፀም የድጋፍና ክትትል ስራ ታህሳስ 26/2018 አጠናቋል።
ቡድኑ በድጋፍና ክትትሉ በርካታ ጠንካራና ክፍተት የታየባቸው አፈጻጸሞችን የለየ ሲሆን በ26/04/2018 ዓ.ም የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባና የከንቲባ ኮሚቴ አባለት በተገኙበት መድረክ ግኝቶቹን አቅርቧል።
ከተማ አስዳደሩ አመራም በድጋፍና ክትትሉ የተስተዋሉትን ጥንካሬወች ለማስቀጠል በእጥረት የተለዩ ተግባራትን በቀጣይ ወራት ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ለማስተካከል ቃል በመግባትና አቅጣጫ በመስጠት ውጤታማ ድጋፍ ማድረግ ተችሏል::
Researching, innovating, influencing”
Website:-http://anrsbopd.gov.et
Telegram:-https://t.me/planpdb2014
YouTube channel: – https://www.youtube.com/@ANRSBOPD-2014
Instagram :- https://www.instagram.com/plan_and_development_bureau/
x-account:- https://x.com/logout
gmail address:- plananddevelopmentbureau@gmail.com

No responses yet