የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕላን እና ልማት ቢሮ በሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር 6 መምሪያዎች ላይ ሲያካሂደው የነበረውን የድጋፍና ክትትል ስራ ተጠናቀቀ።
++++
ታህሳስ 28/2018-ባህር ዳር (ፕላንና ልማት ቢሮ) ፕላንና ልማት ቢሮ ከታህሳስ 24/2018 ዓ.ም ጀምሮ በሰሜን ሸዋ ክላስተር ያሰማራው የድጋፍና ክትትል ቡድን በዞን አስተዳደሩ በስድስት ተቋማት ማለትም ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ፣ ግብርና፣ ትምህርት ፣ ጤና እና ባህልና ቱሪዝም መምሪያ እና ማዕድን መምሪያ ተገኝቶ ሲያካሂደው የቆየውን የዴስክና የመስክ የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት እቅድ አፈፃፀም የድጋፍና ክትትል ስራ ታህሳስ 27/2018 አጠናቋል።
የድጋፍና ክትትል ቡድኑ በርካታ ጥንካሬና የአፈጻጸም ክፍተት የታየባቸውን ተግባራት የለየ ሲሆን በ27/04/2018 ዓ.ም የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ፣ም/አስተዳዳሪ፣ የፓርቲ አመራሮች እንዱሁም ሁሉም የዞን መምሪያ ኃላፊዎች በተገኙበት መድረክ ግኝቶቹን አቅርቦ ውይይት ተደርጎባቸዋል።
የዞኑ አመራርም የተደረገው ድጋፍ ጠቃሚ፣ድክመትና ጥንካሬወችን በግልጽ ያሳየ እንደነበር ግልጾ፤ ቡድኑ ባቀረባቸው ግኝቶች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ካደረገ በኋላ በድጋፍና ክትትሉ የተስተዋሉትን ጥንካሬዎች የበለጠ አጠናክሮ ለማስቀጠል እና በክፍተት የተስተዋሉትን አፈጻጸሞች ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ለማስተካከል ቃል የገባ ሲሆን፤ ተቋማት በቀጣይ ቀሪ ወራት ለእቅዶቻቸው ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩና ውጤት እንዲያስመዘግቡ አቅጣጫ በመስጠት ውይይቱ ተጠናቋል::
Researching, innovating, influencing”
Website:-http://anrsbopd.gov.et
Telegram:-https://t.me/planpdb2014
YouTube channel: – https://www.youtube.com/@ANRSBOPD-2014
Instagram :- https://www.instagram.com/plan_and_development_bureau/
x-account:- https://x.com/logout
gmail address:- plananddevelopmentbureau@gmail.com

No responses yet